"በአዲስ አበባው ፍንዳታ የሞቱት ኢትዮጵያዊያን ናቸው"
በአዲስ
አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ሩዋንዳ ሰፈር የደረሰውን ፍንዳታ አስመልክቶ ኢህአዴግ ያሰራጨውን ዜና የሚቃረኑ መረጃዎችና
አስተያየቶች ቀረቡ። ለኢህአዴግ ቅርበት ያላቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች የድጋፍ አስተያየት ሲሰጡ ዶ/ር መረራ “አትፍቶ
ጠፊ አጥፍቶ ይጠፋል እንጂ በሜዳ ዝም ብሎ አያጠፋም” ሲሉ ጥርጣሬ እንዳላቸው ተናግረዋል። የትግራይ ህዝብ
ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ትህዴን/ በፍንዳታው የሞቱት ኢትዮጵያውያን ናቸው ሲል ስም ገልጾ የኢህአዴግን ዜና
አጠጥሎታል።
በፓርላማ አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ የጠየቁት ከኢህአዴግ ጋር
ግንኙነት እንዳላቸው የሚታሙ ፓርቲዎች “የጸረ ሽብርተኞች አዋጅ ሊጠናከርና ሊጠብቅ ይገባል” ሲሉ ተደምጠዋል።
የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ያነጋገራቸው የኢራፓ፣ የኢሴዳፓ፣ ቅንጅትና አዲአን ተወካዮች በየተራ የኢህአዴግን ዜና
የሚቃወሙና በጥርጣሬ የሚመለከቱትን አውግዘዋል። በወቅቱ የቴሌቪዥን ጣቢያውም አንድነትና የሰማያዊ ፓርቲ ጠርተውት
በነበረው ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ “የጸረ ሽብርተኛነት አዋጅ ለሌላ ተግባር መዋሉን እንቃወማለን” በማለት
የተቃውሞ ድምጻቸውን ሲያሰሙ በማሳየት ዜናውን ለማጀቢያነት ተጠቅሞበት ነበር።
በግል አስተያየታቸውን የተጠየቁት ዶ/ር መረራ ጉዲና በቴሌቪዥን
መስኮት ቀርበው “ብዙዎች፣ እኔም ጓደኞቼም በጥርጣሬ ነው ያየነው” ሲሉ ከተቆረጠው ንግግራቸው ተደምጧል። ዶ/ር
መረራ “አጥፍቶ ጠፊ አጥፍቶ ይጠፋል እንጂ በሜዳ ዝም ብሎ ራሱን አያጠፋም” ካሉ በኋላ “ስለዚህ እውነት
ተደርጓል?” የሚለው ትልቁ ችግርና የጥርጣሬው መነሻ እንደሆነ አመልክተዋል።
ስለዚህ በሚል ድምዳሜ “ሰው አንዳንድ ጊዜ የኢትዮጵያ መንግስት ለራሱ ፖለቲካ ብሎ የሚያደርገው ያው የለመደው ስራ ነው” እንደሚል ዶ/ር መረራ በተቀነጨበው አስተያየታቸው ሲናገሩ ተሰምቷል። በተቃራኒ ከላይ በስም የተዘረዘሩት የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ ኢትዮጵያ የሽብር ጥቃት ኢላማና የአልሸባብ ስጋት ላይ ያለች አገር በመሆኗ ኢህአዴግ ህዝብን የመጠበቅና ደህንነትን የማስጠበቅ አደራ ስላለበት እነሱን ጨምሮ እንዲጠብቃቸው ጥሪ አቅርበዋል።
ስለዚህ በሚል ድምዳሜ “ሰው አንዳንድ ጊዜ የኢትዮጵያ መንግስት ለራሱ ፖለቲካ ብሎ የሚያደርገው ያው የለመደው ስራ ነው” እንደሚል ዶ/ር መረራ በተቀነጨበው አስተያየታቸው ሲናገሩ ተሰምቷል። በተቃራኒ ከላይ በስም የተዘረዘሩት የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ ኢትዮጵያ የሽብር ጥቃት ኢላማና የአልሸባብ ስጋት ላይ ያለች አገር በመሆኗ ኢህአዴግ ህዝብን የመጠበቅና ደህንነትን የማስጠበቅ አደራ ስላለበት እነሱን ጨምሮ እንዲጠብቃቸው ጥሪ አቅርበዋል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ስሙ የሚነሳውና በታጣቂ ሃይሉ ፈርጣማነት
የሚታወቀው የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ትህዴን/ በቦሌ ክፍለ ከተማ በቤት ውስጥ ፈነዳ በተባለው ፈንጂ
ህይወታቸው እንዳለፈ የተገለጸው ሁለት የሶማሌ ዜጎች አይደሉም ሲል ከሁሉም ወገን የተሰራጨውን ዜና በዜሮ አጣፍቶታ።
በፈንጂው የሞቱት ሁለት ሰዎች ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን ስማቸውም “ምክትል ኢንስፔክተር ሞላ መላኩ የተባሉ የፖሊስ
አባልና አቶ ሞገስ አስቻለው የተባሉ ሲቪል ናቸው” ሲል የገለጸው ትህዴን የሟቾቹ ስም በመታወቂያ መረጋገጡን
አመልክቷል።የመታወቂያውን ቅጂ ግን በገጹ አላተመም። ከአደጋው ጋር በተያያዘ በስፍራው ታይታችኋል በሚል በርካታ
የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት መታሰራቸውን በመግለጽ የሶስት እስረኞችን ስም ይፋ ያደረገው ኦክቶበር 19 ቀን 2013
በራሱ ኦፊሳላዊ ድረገጽ ላይ ነው። ኢህአዴግም ቢሆን ሞቱ የተባሉትን ሰዎች ይህ ዜና እስከተጻፈበት ቀን ድረስ
በሰነድ አስደግፎ አላቀረባቸውም።
በሌላ በኩል ኦክቶበር16 ለንባብ የበቃው ሪፖርተር ጋዜጣ ጥቅምት
3ቀን 2006ዓ.ም. በቦሌ ክፍለ ከተማ ሩዋንዳ ማዞሪያና ቦሌ ሚካኤል መግቢያ አካባቢ በቦምብ ፍንዳታ ሕይወታቸው
ያለፈው ሁለት ሶማሊያውያን ሽብርተኞች መሆናቸውን ማረጋገጡን፣ የፌዴራል ፖሊስ የፀረ ሽብር ግብረ ኃይል ማስታወቁን
ዘግቧል።
SOURCE, GOLGUL FOR MORE INFORAMATION VISIT THE SITE
No comments:
Post a Comment