Saturday, August 3, 2013

ግመል ሰርቆ ማጎንበስ አይቻልም

meles at g20
የአሜሪካ የውጭ ዕርዳታ ድረገጽ መረጃ እንደሚለው ከሆነ ከሰሃራ በታች ከሚገኙ አገራት መካከል የአሜሪካንን ዕርዳታ በመቀበል ቀዳሚነቱን ሥፍራ የያዘችው ኢትዮጵያ ነች፡፡ (http://www.foreignassistance.gov/)
የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ ወይም በጀት ከተደረገው ውጪ የሚሰጠውን ተጨማሪ ዕርዳታና ድጎማ ሳይጨምር ከ2009 – እስከ 2012 ባሉት ዓመታት ብቻ ኢትዮጵያ ከ3.3ቢሊዮን ዶላር በላይ (በወቅቱ ምንዛሪ ከ60ቢሊዮን ብር በላይ) ዕርዳታ ተቀብላለች፡፡
ገንዘቡ የሚሠጠው ሰላምና ደኅንነት ለማስጠበቅ፤ ለዴሞክራሲ፣ ሰብዓዊ መብቶችና መልካም አስተዳደር፤ ለጤና፤ ለትምህርትና ማኅበራዊ አገልግሎቶች፤ ለኢኮኖሚ ልማትና ለአካባቢ ጥበቃ እንደሆነ ድረገጹ ያስረዳል፡፡ (በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ የተቀናበረ – AP Photo/Steve Parsons/pool)
Source, Golgul Web site



እንደራሴ ስሚዝ አዲስ አበባ ሊሄዱ ነው የኢህአዴግ መልስ በጉጉት ይጠበቃል


chris smith
አሜሪካና ሌሎች ለሰብአዊ መብት መከበር ዋጋ የሚሰጡ አገሮች በሙሉ በ”አዲስ አበባው” አገዛዝ ላይ ጠንካራ አቋም መያዛቸውን ያለ አንዳች ማወላወል ማሳየት እንደሚገባቸው አሳስበው የነበሩት ኮንግረንስ ማን ክሪስ ስሚዝና ባልደረባቸው እንደራሴ ኬረን ባስ አዲስ አበባ እንደሚገቡ ተጠቆመ። በሰኔ (ጁን) ወር “… የአሜሪካ መንግስትም ሆነ ሌሎች የምዕራብ አገራት፣ ኢህአዴግ ኢትዮጵያዊያን ላይ እየፈጸመ ያለውን ተግባር በመረዳት አቋማቸውን በግልጽ ማስቀመጥ ይገባቸዋል” የሚል ጥሪ ያስተላለፉት ክሪስ ስሚዝ አዲስ አበባ መምጣት ኢህአዴግን እንዳሳሰበው ለማወቅ ተችሏል።