ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሠላማዊ ትግላቸውን አድማስ ለማስፋት ከወትሮው በተሻለ ሁኔታና መተጠናከረ መንገድ በመላ ኢትዮጵያ ሲንቀሳቀሱ ነበር፡፡ ይህ እንቅስቃሴያቸው ግን ከመንግሥት የሕግ ጥበቃ ከማጣቱ የተነሳ ፓርቲዎቹ ከፍ ያለ ጉዳት እየደረሰባቸው ነው፡፡ ይህንን ሕገ-ወጥነት ሕዝቡ እንዲያውቀውና እንዲታገለው ይህንን መግለጫ ማውጣት አለስፈላጊ ሆኗል፡፡
It encourage all Ethiopians to stand together to overthrow undemocratic regime from motherland Ethiopian.
Wednesday, September 18, 2013
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና ሌሎች በእስር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ ተጠየቀ።
መስከረም ፮(ስድት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አዲስ ከዓመት በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ ለ14 ወራት በቃሊቲ እስርቤት ከታሰሩ በኋላ ተፈተው የወጡት ስዊድናውያን ጋዜጠኞች ማርቲን ሺቢ እና ዩዋን ፐርሹን እንዲሁም ዓለምዓቀፍ የሰብዓዊና የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅቶች ተወካዮች፡ ጋዜጠኞችና በስዊድን የሚኖሩ በመቶ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን እና ስዊድናውያን አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባዘጋጀው ደብዳቤ ላይ ፊርማቸውን በማኖር ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ የታሰሩ ጋዜጠኞችን እንዲፈቱ ጠይቀዋል።
ስዊድናውያን ጋዜጠኞች ኢትዮጵያ ውስጥ ያሳለፉትን የእስር ህይወት የሚተርከውን እና በቅርቡ ለህትመት የበቃው 438ቱ ቀናት የሚለው መጽሃፋቸው ኢትዮጵያውያንን የህሊና እስረኞችን ለማስታወስ በተዘጋጀው ዝግጅት ላይ ይፋ እንዲሆን የወሰኑት በሽብርተኝነት ወንጀል ተከሰው በከፍተኛ ስቃይ ለሚንገላቱት ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች እና ሌሎች የህሊና እሰረኞች የገቡትን ቃል ለማደሰ እንደሆነ በዝግጅቱ ላይ ለተገኙ ተሳታፊዎች ገልጸዋል።
734 ሚሊዮን 600 ሺ ብር የመዘብሩ የስራ ሃላፊዎች አለመቀጣታቸውን መረጃዎች አመለከቱ
አዲስ ከስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሺን የተገኝው መረጃ እንደሚያመለክተው ከተለያዩ የፌደራል መስሪያ ቤቶች 734 ሚሊዮን 6 መቶ ሺ ብር የመዘብሩ የስራ ሃፊዎች በተጣራ መረጃ ክስ ቢመሰረትባቸውም የውሳኔ ቅጣት እንዳልተላለፈባቸው ታውቋል።
ለረጅም ጊዜ በተደረገ ምርመራ ተጣርቶና መስረጃ ተገኝቶባቸው ከ2004 ዓም ጀምሮ ክስ የተመሰረተባቸው የተለያዩ የሙስና ወንጀሎች የውሳኔ ሀሳብ እንዳልተላለፈባቸው ከመሰሪያ ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን ላይ 94 ሚሊዮን 300 ሺ ብር ከትምህርት ተቋማት ግንባታ ጋር በተያያዘ የተፈጸመ የሙስና ወንጀል ምርመራ ተጠናቆ ክስ ቢመሰረትም በቂ ውሳኔ ሳያገኝ ቀርቷል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የግል ባንኮችን አካውንት አገደ
በአገሪቱ የባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ የአንበሳውን ድርሻ በያዘው መንግሥታዊው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውስጥ አካውንት ያላቸው የግል ባንኮች አካውንታቸውን እንዳያንቀሳቅሱ ታገዱ፡፡
ከአንዳንድ የግል ባንኮች የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውስጥ ያላቸውን አካውንት እንዳያንቀሳቅሱ የተገለጸላቸው፣ አካውንታቸው ባለበት ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ በኩል በተጻፈ ደብዳቤ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይህንን ዕርምጃ ለመውሰድ የተገደደበት ምክንያት ግልጽ ባይሆንም፣ ከሰኞ መስከረም 6 ቀን 2006 ዓ.ም. ጀምሮ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውስጥ የነበራቸውን አካውንት ማንቀሳቀስ የማይችሉ መሆኑ እንደተገለጸላቸው ታውቋል፡፡
ጉዳዩን በተመለከተ ያነጋገርናቸው የግል ባንኮች ኃላፊዎች እንደጠቆሙት፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዕርምጃ ያልተጠበቀ እንደሆነባቸው ነው፡፡ ‹‹ሆኖም የእኛን የተወዳዳሪዎቹን አካውንት እንዳይንቀሳቀስ ሲያደርግ ቢያንስ ምክንያቱን ሊገልጽ ይገባ ነበር፤›› ይላሉ፡፡ የግል ባንኮቹ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውስጥ አካውንት የከፈቱበት ዋነኛ ዓላማ አንዳንድ ክፍያዎችን በቀጥታ ከዚያ ለመክፈል እንዲያስችላቸው እንጂ ሌላ ዓላማ የሌለው መሆኑን የግል ባንኮች ኃላፊዎች ያስረዳሉ፡፡
አንድ ባንክ በሌላ ባንክ ውስጥ አካውንት ሊከፍት የሚችለው በሥራ ውስጥ የሚያጋጥሙ ክፍያዎችን በቀላሉ ለመፈጸምና የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት ታስቦ ነው በማለት የሚያስረዱት የግል ባንኮች ኃላፊዎች፣ ይህ በባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ የተለመደ አሠራር ቢሆንም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወደዚህ ዕርምጃ መግባቱ እንቆቅልሽ እንደሆነባቸው አስረድተዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት 19 ባንኮች በሥራ ላይ ሲሆኑ፣ ሦስቱ የመንግሥት 16ቱ ደግሞ የግል ናቸው፡፡ የግሎቹም ሆነ የመንግሥት ባንኮች በጥምረት የሚያስተሳስራቸው የኢትዮጵያ ባንኮች ማኅበር ሲሆን፣ አሁን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወሰደውን ዕርምጃ በማኅበራቸው በኩል ለመነጋገር ሐሳብ ያላቸው መሆኑንም የተገኘው መረጃ ያስረዳል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንታቸው እንዳይንቀሳቀስ ወሰነ ማለት ግን በአካውንታቸው ውስጥ ያለውን ገንዘብ ያግዳል ማለት እንዳልሆነ ተጠቅሷል፡፡
አንዳንዶቹ የግል ባንኮች አካውንቱ ለምን እንዲታገድ እንደተደረገ ላቀረቡት ጥያቄ ማብራሪያ ባለማግኘታቸው በሁኔታው ማዘናቸውን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንዳንድ ኃላፊዎችን ለማነጋገር የተደረገው ሙከራ ካለመሳካቱም በላይ፣ በሞባይል ስልካቸው በጽሑፍና በድምፅ የተላለፈላቸውን ጥያቄ ለመመለስ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡
SOURCE, REPORTER

Subscribe to:
Posts (Atom)