Thursday, November 7, 2013

የመረጃ መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) በከፍተኛ ሥልጣንና ጉልበት በድጋሚ ሊቋቋም ነው


በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ኮምፒዩተሮች ላይ ምርመራ ያካሂዳል
insa ethiopia


ባለፉት በርካታ ዓመታት በሥራ ላይ የሚገኘውን የመረጃ መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ከፍተኛ ኃላፊነትና ጉልበት የሚሰጥና በድጋሚ እንዲቋቋም የሚያደርግ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ፡፡
በፓርላማው ቋሚ ኮሚቴዎች ተጨማሪ ውይይት እየተደረገበት የሚገኘው ይህ ረቂቅ አዋጅ፣ በቀጣዮቹ ጥቂት ሳምንታት ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ረቂቅ አዋጁ ከፀደቀ በኋላ ኤጀንሲው በድጋሚ የሚዋቀር ሲሆን የአገሪቱ የፋይናንስ ተቋማትን፣ ብሔራዊ የኤሌክትሪክ ኃይል መረብን፣ በግንባታ ላይ የሚገኘውን አገራዊ የባቡር ትራንስፖርት መረብን፣ ወታደራዊ የኮምፒዩተር ሥርዓትንና ሌሎች ኮምፒዩተራይዝድ የሆኑ መሠረተ ልማቶችን በኮምፒዩተር አማካይነት ከሚቃጡ ጥቃቶች የመጠበቅ ኃላፊነት ይኖረዋል፡፡
የረቂቅ አዋጁ አባሪ ሰነድ ሆኖ የቀረበው ማብራሪያ እንደሚያስረዳው፣ በአገሪቱ በሚታየው የኢኮኖሚ ዕድገት ሳቢያ በርካታ የአገሪቱ እንቅስቃሴዎችና አገልግሎቶች የኮምፒዩተርና የኮምፒዩተር መረብ ጥገኛ መሆናቸው፣ እንዲሁም የዓለም ነባራዊ ሁኔታ አዋጁ እንዲዘጋጅና ኤጀንሲውን በድጋሚ እንዲቋቋም ለማድረግ ምክንያቶች ናቸው፡፡
የአገሪቱ የኤሌክትሪክ ኃይል፣ የባቡር፣ የአቪዬሽን፣ የውኃ አቅርቦትና ሌሎች ኮምፒዩተራይዝድ በሆኑ ሥርዓቶች እየተመሩ መሆኑን በአብነት ያነሳል፡፡ በምሳሌነትም የአገሪቱ የኃይድሮ ኤሌክትሪክ ማመንጫ፣ ማስፋፊያና ማሠራጫ ሥርዓቱ በኮምፒዩተራይዝድ ሥርዓት የሚመራ በመሆኑ፣ በዚህ ሥርዓት ላይ የሚደረግ የኮምፒዩተር ጥቃት የአገሪቱን የኃይል አቅርቦት ከማቋረጡም በተጨማሪ፣ ኃይል አመንጪ ግድቦች ውስጥ የተጠራቀመ ውኃ ፍሰቱ እንዲዛባ በማድረግ መሠረተ ልማቱ ሙሉ በሙሉ እንዲወድም ሊያደርግ እንደሚችል ይገልጻል፡፡
በተመሳሳይ በአገሪቱ እየተገነባ ያለው የባቡር ትራንስፖርት በኮምፒዩተር ሥርዓት ቁጥጥር የሚደረግበት በመሆኑ፣ በዚህ ሥርዓት ላይ ጥቃት በማድረስ ባቡሮች ከመስመራቸው ውጪ እንዲንቀሳቀሱና አደጋ እንዲደርስባቸው ምክንያት ሊሆን ይችላል በማለት ያስረዳል፡፡
በመሆኑም ኤጀንሲውን በድጋሚ በማዋቀር ሰፊ የደኅንነት ኃላፊነቶችን እንዲወጣ ማድረግ ተገቢ መሆኑን ይገልጻል፡፡ ይህንን ኃላፊነት ኤጀንሲው እንዲወጣ በኤጀንሲው ሥር ብሔራዊ የኮምፒዩተር ድንገተኛ አደጋ ምላሽ መስጫ ማዕከል እንዲቋቋም የሚያስችል አንቀጽ በረቂቅ አዋጁ ተካቷል፡፡ ማዕከሉ ሊደርሱ የሚችሉ ጥቃቶችን ለመለየት፣ ጥቃቶችን ቀድሞ በመተንተን ለማወቅ፣ ጥቃት ሲከሰት በብቃት መግታት ወይም መጠነ ሰፊ ጉዳት ሳያስከትል መቆጣጠርና ሌሎችንም ተግባራት የሚያከናውን ይሆናል፡፡
ኤጀንሲው ይህንን ኃላፊነቱን በአግባቡ ለመወጣት እንዲያስችለው የደኅንነት ኦዲት ማድረግ የሚያስችል ሥልጣን በረቂቁ ተካቷል፡፡ የደኅንነት ኦዲት ማለት ኮምፒዩተርን መሠረት ባደረገ ቁልፍ መሠረተ ልማት ላይ ተጋላጭነትን ለማወቅ የዘልቆ ገብ ፍተሻ ተግባራትን ማከናወንና አገራዊ የኢንፎርሜሽን ፖሊሲና ስታንዳርድን መሠረት በማድረግ፣ የተቋማቱን የኢንፎርሜሽን ደኅንነት ሥርዓት በመገምገም የእርምት ዕርምጃ እንዲወስዱ ማድረግ የሚል ትርጓሜ በረቂቁ ተሰጥቶታል፡፡
ኢንፎርሜሽን (መረጃን) መሠረት ባደረጉ ቁልፍ መሠረተ ልማቶች ወይም ሥርዓቶች ላይ እንዲሁም በዜጎች ሥነ ልቦና ላይ የሚሰነዘሩ የሳይበርና የኤሌክትሮማግኔቲክ ጥቃቶችን ለመከላከል አስፈላጊ አፀፋዊ ዕርምጃ የመውሰድ ኃላፊነት ይኖረዋል፡፡ የሳይበርና የኤሌክትሮማግኔቲክ ጥቃቶች የሚባሉት የኢንተርኔት ሬዲዮ ወይም ቴሌቪዥን፣ የቴሌቪዥንና የሬዲዮ አገልግሎቶች፣ የማኅበራዊ ሚዲያዎች (ማለትም ፌስቡክን የመሳሰሉ)፣ ዌብሳይቶች፣ ብሎጐችንና የመሳሰሉትን በመጠቀም የሚተላለፍ መሆኑን የአዋጁ ማብራሪያ ያትታል፡፡
በእነዚህ የመገናኛ አውታሮች የሚተላለፉ መረጃዎች ለማኅበራዊ፣ ለፖለቲካዊና ለኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ያላቸው ፋይዳ ግዙፍ ቢሆንም በተቃራኒው ለጦርነት ቅስቀሳ፣ የአገርን ገጽታ ለማጉደፍ፣ ፀረ ልማት ፕሮፓጋንዳዎችንና ኢኮኖሚያዊ ትንበያ (ስፔኩሌሽን) ማሠራጨት መጠቀሚያ ሊሆኑ እንደሚችሉ ማብራሪያው ይገልጻል፡፡ በመሆኑም የአዋጁን መፅደቅ ተከትሎ የተጠቀሱትን ጉዳት ያላቸውን መረጃዎች ኤጀንሲው የማክሸፍ ሕጋዊ ሥልጣን አለው፡፡
ኢንፎርሜሽንና ኮምፒዩተርን መሠረት ያደረጉ ቁልፍ መሠረተ ልማቶች ደኅንነትን ለማረጋገጥ ሲባል ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ በማውጣት የጥቃት ሰለባ ወይም መነሻ ናቸው ተብለው በተጠረጠሩ ኮምፒዩተሮች ወይም መሠረተ ልማቶች ላይ አስፈላጊውን ምርመራ ማካሄድ፣ ሌላው በረቂቅ አዋጁ የተካተተ የኤጀንሲው የወደፊት ኃላፊነት ነው፡፡ (ምንጭ፡ ሪፖርተር)
Source, Golgul website

ዕርቅን የሚፈልግና የሚቀበል በራሱ የሚተማመንና ደፋር ነው

(አንዱ ዓለም ተፈራ፤ የእስከመቼ አዘጋጅ)
strong


ከዝግጅት ክፍሉ፡ “በህወሃት ውስጥ የዕርቅ ሃሳብ መነሳቱ ተሰማ” በሚል ርዕስ ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ላቀረበው የዜና ዘገባ አቶ አንዱ ዓለም ተፈራ የሚከተለውን የአጸፋ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ በቅድሚያ ጊዜያቸውን ወስደው ይህንን ምላሽ ስለጻፉ እያመሰገንን ይህንን ዓይነቱን ባህል ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሚያደፋፍር መሆኑን እንወዳለን፡፡

በኢትዮጵያዊያን ዘንዳ፤ ይቅር ለፈጣሪ ብሎ ከተጣሉት ጋር እንዲታረቁ፤ ከልበ ሙሉዎች፣ ከባህል አካሪዎችና ለነገ ግምት ካላቸው ሰዎች ይጠበቃል። እናም አመዛዛኝ የሆኑ፤ አክብሮት፣ ርጋታና ፍቅር ያላቸው፤ ለእርቅ ምን ጊዜም በራቸው ክፍት ነው። አጉል የሆኑት ደግሞ፤ እኔ ስህተት አልሠራም፣ እኔ ምን ጊዜም ትክክለኛ ነኝ፤ ስለሚሉና ሌላው ሁሉ ለነሱ ሰግዶ እንዲልመጠመጥ ስለሚፈልጉ፤ ለእርቅ በራቸው ዝግ ነው። አጉል የሆኑ ማለት፤ እብሪተኞች፣ ፈሪዎች፣ በራሳቸው የማይተማመኑ፣ የግልና የአሁን ሕይወታቸውና ጥቅማቸው እንጂ፤ የኅብረተሰብ ወይንም የሀገር ጉዳይ የማይዋጥላቸው ናቸው። ትናንት በጎልጉል ገፅ፤ በህወሃት ውስጥ የዕርቅ ሃሳብ መነሳቱ ተሰማ – “የኢህአዴግ የአፈና ገመድ ነትቧል፣ ድርጅቱ ተናግቷል” በሚል ርዕስ አዘጋጆች የጻፉትን ደጋግሜ ተመለከትኩትና እኔ ይኼን በሚመለከት፤ የትም የሚደርስ አይደለም በማለት ሀሃስቤን እንደሚከተለው አቅርቤአለሁ።
በኢትዮጵያ ያለው የፖለቲካ ሀቅ ለማንኛውም ሰው ዓይን የሚያስፈጥጥ፣ የሚረብሽና እረፍት የሚነሳ ነው። ይኼን በምንም መንገድ ቢያዩት፤ የነገውን አስፈሪ መጪ ሊያስበረግገው አይችልም። አስፈሪ ነገ ከፊታችን ላይ ተገትሯል። እንግዲህ ጥያቄዎቹ፤ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ይኼን እንዴት ሊያየው ይችላል? ነው። ማየቱ ብቻ ሳይሆን ምን ያደርጋል? ነው።
አንድ ግልፅ መሆን ያለበት ሀቅ አለ። ለዚህ ሁኔታ ተጠያቂው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ነው። ይህን ግን ግንባሩ አይቀበለውም። እናም መፍትሔ ፍለጋ የሚሮጠው ከዚህ ተነስቶ አይደለም። እናም ዕርቅ አይዋጥለትም። በተመሳሳይ መንገድ፤ አፄ ኃይለ ሥላሴ ለሕዝቡ ትንሽ መፈናፈኛ የሥልጣን መንገድ አለመክፈታቸውን፤ መንግሥቱ ኃይለ ማርያም ከሱ ሌላ አዋቂና መፍትሔ ሠጪ የለም ብሎ ማመኑን፤ በተመሳሳይ ምንገድ ደግሞ መለስ ዜናዊ የዚሁ ቅጂ መሆኑን ማጤን ይኖርብናል። ሶስቱም ገዥዎች ከራሳቸው በላይ ነፋስ ብቻ ባይ እንደነበሩ ሁላችን እናውቃለን።
አንዳንዶቻችን የራሳችንን ኃላፊነት ወደ ሌላው በማሻገር፤ ህወሃት በራሱ ፈርሶ ወይንም በፈቃዱ ሥልጣን ሊያጋራ እንደሚችል ማስረጃው ሳይሆን ምኞቱ አለን። ደግ! ምኞት ብለን መቀበል አንድ ነገር ነው። ምኞት ብቻ ነው ብለን መቀበል አለብን። ከዚያ አያልፍም። በርግጥ የሕዝቡ እየደፈረ መምጣትና በተለያዩ ቦታዎች የሚነሱት ጥያቄዎች የትግሬዎችን ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት መሪዎች ሊያቁነጥንጥ ይችላል። መቀመጫዎቻቸውን ከማደላደል ያለፈ ግን፤ የሚያደርጉት እንደሌለ መረዳት አለብን። ከደረስብን ግፍና በደል ተነስተን፤ ምኞታችን በዝቶ አስተሳሰባችንን እየጋረደው፤ ምኞታችንን ሀቅ እያደረግን የምንዋዥቅ ሞልተናል። ግን ታሪክ የሚያስተምረን፤ ከእባብ እንቁላል እርግብ እንዳንጠብቅ ነው።
በትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት መሪዎች መካከል ዕርቅ ለውይይት ሊነሳ ይችላል። ይኼን መቼም አይደረግም ብዬ አፌን ሞልቼ መናገር አልችልም። በመካከላቸው አንድነት ስለሌለ፤ አንዳንዶቹ ያገኙትን ጥቅም ይዘው የተደላደለ የወደፊት ኑሮ ከፊታቸው ብልጭ ሊልባቸው ይችላል። እነዚህ ግን አቅራቢዎቹ ግለሰቦች ብቻ ናቸው። ወሳኙ ደግሞ ተሰባስበው በአንድነት የሚስማሙበት ብቻ ነው። እናም ማተኮር ያለብን፤ የጠቅላላ ስብስቡ ቅኝት ላይ ነው። የጠቅላላ ስብስቡ ቅኝት ደግሞ ከራሱ ታሪክና ከሌሎች መሰሎቹ ታሪክ የተጻፈ ስለሆነ ማወቁ አይቸግርም። ታሪክ ታስተምራለች ሲባል፤ ማገናዘቡን ለኛ ትታ ነው። ከታሪክ የማንማር ከሆን፤ አሁንም በዚያው ስንዳክር ለወጪዎቹ በሽታችንን እናተላልፍላቸዋለን። ትጥቅ መፍታት እንዳይሆን መገንዘብ አለብን።
እርቅ ወርዶ ሀገራችን በሰላም የወደፊቷን የምትጀምር ከሆነ፤ ከማንም በማያንስ ደረጃ ደስተኛ እሆናለሁ። በምኞት ፈርስ ግን መጋለቡን እስከዛሬ አድርገነዋልና የዚያ ፈረስ ጥላውም ከኔ ጋር የለም። ፈረሱ ደክሞት ሕይወቱን ጨርሶ ሞቷል። ጥላውም አብሮ ተቀብሯል። የሀገራችን አደጋ ከባድ ነው። የተመሰቃቀለ ነው። እንዲያው አንድ ቀን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ተነስቶ ከዛሬ በኋላ ሁሉ ነገር ተለውጧል! የሚልበትና የሚቀየርበት እውነታ ገና መጻፊያ ቀለሙ አልተበጠበጠም።
እንዲህ ነው። የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት መሪዎች ዕርቅ ይፈልጋሉ ብለን ስንጀምር፤ ከኛ ምኞትና እምነት ሳይሆን መነሳት ያለብን፤ ከነሱ እምነትና እውነታ ነው። መመልከቻ መነፅራችን የነሱ መሆን አለበት። ለምን ይፈልጋሉ? በነሱ እምነት፤ ጠንካራ ተቃዋሚ የለም። ሥልጣኑ ሁሉ በጃቸው ነው። ሀብቱ ሁሉ በጃቸው ነው። ጉልበቱ ሁሉ በጃቸው ነው። መንግሥታዊ መዋቅሩ ሁሉ በጃቸው ነው። የውጭ ሀገር መንግሥታት ሁሉ የሚያውቋቸው እነሱን ብቻ ነው። ብዙ የድርጅት አባላት ያሏቸው እነሱ ብቻ ናቸው። በሌላ በኩል እኛ ይኼ ሁሉ ገለባ እንደሆነ እናውቃለን። ለዚህ ነው፤ እንዲህ ስለሆነ፣ ያ በዚያ ሰለመጣ . . . እያልን የምንደራርተው። ይኼንን የተረዱ፣ የሚይውቁትና የሚቀበሉት ቢሆን ኖሮ፤ ብዙ አምባገነን መሪዎች ቀድመው እርምጃ ይወስዱ ነበር። አላደረጉም። የኛዎቹ አምባገነኖች ከሌሎች ተለይተው አዋቂና ጥንቃቄ ይወስዳሉ ማለት፤ የምኞትን ቦታ ለእውነታ ማስረከብ ነው። አልፎ ተርፎም፤ ማንም ሳይጠይቀን ራሳችን ራሳችንን ትጥቅ እያስፈታን እንዳይሆ አፈራለሁ።
አሁንም አንድ ታሪክ የሚያስተምረንን ቁም ነገር እዚህ ላይ ልጥቀስ። እንደሌሎቹ አምባገነኖች ሁሉ፤ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት መሪዎች ሁሉ፤ ለሁሉም ጥያቄዎች ያላቸውና የሚሠጡት መልስ፤ በጉልበት መደምሰስ ነው፤ ከሕዝቡም በኩል ይምጣ ከራሳቸው መካከል። ይልቁንስ ኢትዮጵያዊያን በአንድ ሆነን፤ አንድ አጀንዳ ብቻ ይዘን፤ ከሕዝቡ ጎን በመሠለፍ፤ እውነተኛ መፍትሔ የሚመጣበትን መንገድ አብረን እንፈልግ።
የኢትዮጵያን ነገ የሚወስነው፤ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት የሚያደርገው ወይንም የማያደርገው ሳይሆን፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚተገብረውና የሚጽፈው ብቻ ነው። የየካቲት ፲፱፻፷፮ ዓመተ ምህረት ታሪክ የኢትዮጵያ ሕዝብ መነሳት እንጂ፤ የንጉሠ ነገሥት ዝም ማለት አይደለም። የደርግም የመጨረሻ ታሪክ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ እምቢታና የታጠቁ ኃይሎች ደርግን መደምሰስ እንጂ የደርግ ተግባር አልነበረም። አሁንም በድጋሜ፤ የነገው ታሪካችን የኢትዮጵያ ሕዝብ መነሳት እንጂ፤ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ተግባር አይደለም የሚጻፈው። ሲጀምርና ሲጨርስ፤ “የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንድነት ተነስቶ በማመፅ፤ የትግሬዎችን ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ደመሰሰ!” ነው የሚለው።
አስከመቼ
Source, Golgul

Breaking: Four killed in bomb blast as Ethiopia raises security alert


ADDIS ABABA (Reuters) – Four people were killed when a bomb blast tore
 through a minibus in western Ethiopia late on Tuesday, at about the same time
that the government warned of imminent attacks by militants, an official said.
The official, speaking to Reuters on Wednesday, said nobody had claimed responsibility
 for the blast.
Addis Ababa put its security forces on heightened alert on Tuesday night after
 receiving strong evidence that Somalia’s Islamist al Shabaab group was plotting assaults.
It was not clear whether the blast occurred before or after that warning.
“The bomb exploded on Tuesday inside a minibus travelling in Segno Gebeya,”
 government spokesman Shimeles Kemal said, referring to a region bordering Sudan.
“No one has claimed responsibility yet. The case is under investigation.”

Full ETV Report on the Bomb Blast that killed four people


The warning came three weeks after officials said two Somali suicide bombers accidentally
blew themselves up while preparing for an attack on football fans during Ethiopia’s
World Cup qualifying match against Nigeria.

Al Shabaab has warned Ethiopia of revenge attacks for deploying troops inside Somalia
to fight the al Qaeda-linked militants, alongside African Union forces from Uganda,
Burundi and Kenya.
The National Intelligence and Security Service also urged the public on Tuesday to
 inform police if they encountered “suspicious” activity, and urged hotel staff and
 private landlords to verify the identity of visitors.
Al Shabaab gunmen killed at least 67 people in September when they raided a
mall in the neighbouring Kenyan capital of Nairobi.
Addis Ababa says it has foiled several attacks in the past few years planned by domestic
rebel groups and Somali insurgents.
There have also been sporadic explosions in recent years. Thirteen people were wounded
when an explosive device ripped through a bus in the north in 2010, while a bomb
explosion near a court in the capital injured two in 2011.
(Reporting by Aaron Maasho; Editing by Edmund Blair and Hugh Lawson)
Source, Dire Tube