የአፍሪቃ ሕብረት አባል መንግሥታት መሪዎች ሐገሮቻቸዉ ከዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች መዳኛ ፍርድ ቤት አባልነት ሥለመዉጣት አለመዉጣታቸዉ ለመነጋገር በቅርቡ ይሰበሰባሉ።የሕብረቱ ባለሥልጣናት ዛሬ እንዳስታወቁት የዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት አባል የሆኑት የአፍሪቃ ሐገራት ከፍርድ ቤቱ ይዉጡ የሚለዉ ሐሳብ እስካሁን ግልፅ ድጋፍ የለዉም።ይሁንና የኬንያን ፈለግ መከተል የሚሹ አባል መንግሥታት መኖራቸዉ በግልፅ ይታያል።የኬንያ ምክር ቤት ሐገሪቱ «የሮም ስምምነት» ከሚባለዉ ከዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት አባልነት እንድትወጣ በቅርቡ ወስኗል።የዩጋንዳ ባለሥልጣናትም ኬንያን የመከተል አዝማሚያ አሳይተዋል።መሪዎቹ ጥቅምት መጀመሪያ አዲስ አበባ ዉስጥ ለመነጋገር የፈለጉትም የጋራ-የሚሉትን አቋም ለመያዝ ነዉ።ከሐምሳ-አራቱ የአፍሪቃ ሐገራት ሰላሳ-አራቱ የፍርድ ቤቱ አባላት ናቸዉ።ዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት የኬንያን መሪዎች በሰዉ ልጅ ላይ በተፈፀመ ወንጀል ከከሰሰ ወዲሕ ብዙ የአፍሪቃ መሪዎች ፍርድ ቤቱን በዘረኝነት እየወቀሱት ነዉ።
No comments:
Post a Comment