Friday, September 20, 2013

የወያኔ መንግስት ተቃዋሚዎች በመስቀል አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ እንዳያደርጉ ከልክሎ በአዲስ አበባ አካባቢዎች የሚኖሩትን ወጣት ዜጎችን እየያዙ ይገኛሉ ::

የኢአህዴግ መንግስት በታላቅ  ግራ በመጋባት ውስጥ ነው ያላው :: በሀገሪቱም ያሉ ባለ ስልጣኖቸ ስጋት እና ውጥረት ውስጥ እንደሚገኙ አንዳንድ ምንጮች ያስረዳሉ ::በአገሪቷ ላይ የሚኖረው ህዝብም በወያኔ አመራር  በመማረር በአገሪቱ ውስጥ እየተደረገው ነገር ደስተኛ ባለመሆነ ውስጥ ውስጡን በኢአህዴግ መንግስት መገዛትን እያመረረ ይገኛል :: በሀገሪቱ ላየ የሚኖረው ወጣቱ ትውልድም ልቡ ከገዢው ፓርቲ ጋር አይደለም ያለው ::

ይህንንም የወያኔ መንግስት በሚገባ እየተረዳው ያለ ይመስለኘል  በርግጥም ነው የኢትዮጵያ ህዝብ በወያኔ ኢአዲግ መንግስት ላይ ጥላቻውን መግለጥ ከጀመረ ብዙ አመታቶች አልፈውታል ይህ ህዝብ ምን ያክል ይሄን አገዛዝ እንደሚጠላ እና ልቡም አብሮ እንደሌለ በምርጫ 97 ጌዜ በገሐድ ያሳየ ሲሆን ከምርጫ 97 በኋላም ባገኘው አገጣሚ ሁሉ ለወያኔ መንግስት ያለውን ከልብ የሆነ ጥላቻ እያሳየ ይገኛል :: የኢትዮጵያ የወያኔ አገዛዝ መሮታል መንግስትም ህዝቡን በሀይል እና በጉልበት እየገዛ ነው ያለው::  ህዝብን ደግሞ በሀይል እና በጉልበት እየገዙ መኖር ለጊዜው ይቻል ይሆናል ::ነገር ግን አንድ ቀን ግን  የህዝብ ቁጣ እየገነፈለ ሲመጣ ብሶቱም እየባሰ ሲሂድ  እንደ ቱኒዚያ እና እንደ ግብጽ ህዝብ የህዝቡ ቁጣ ገንፍሎ የወጣ ቀን መንግስት ሊቋቋመው የሚችለው አይመስለኝም :: 
 ይህንንም በሀገራችን ኢትዮጵያ ላይ በቅርብ ቀን እንደምናየው ተስፋ አደርጋለው  :: ለዚህም ይመስላል  መስከረም 12 እና መስከረም 19 ቀን  2006 ዓ/ም በአዲስ አበባ ሁለቱ ፓርቲዎች የሰማያዊና የአንድነት ፓርቲዎች የጠሩዋቸውን ሰልፎች ተከትሎ የኢአህዴግ መንግስት በከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ የሚገኘው :: 
የወያኔ ኢአዲግ መንግስት ከትናንትው እለት  ጀምሮ  በተለያዩ በአዲስ አበባ አካባቢዎች  የሚኖሩትን ወጣት ዜጎችን  ሊስትሮዎ፣ ስራ ላይ የተሰማሮትን በጎዳናዎች ላይ እቃዎችን የሚሸጡትን  በፖሊስ የጸጥታ ሀይሎቹ አማካኝነት  እየሰበሰቡና ወደ አልታወቀ ስፍራ እየወሰዱዋቸው ነው።
ለጊዜው የሚታፈሱት ሰዎች ወዴት እንደሚወስዱ ባይታወቅም በትናትናው እለት ኢሳት በዜናው እንደዘገበው  እነዜህ ወጣት የሀገሪቱ ንጹሀን ዜጎች ያለምንም ሀጢያት እና በደላቸው የሰማያዊና የአንድነት  ፓርቲዎቹ ያዘጋጁት ሰልፍ እሲከጠናቀቅ ታግተው ይቆያሉ። ይህም ወያኔ ለጊዜው ያዋጣኛል ብሎ ያሰበው መንገድ ሲሆን ፓርቲዎቹ በጠሩት ሰልፍ ላይም የአዲስ አበባ ወጣተ ህዘብ በነቂስ ወቱ እንደሚሳተፍ እና በመንግስት ላይ የተቃውሞ ድምጹን እንደሚያሰማ የተገነዘበ ይመስላል::
በዛሬው እለት ባገኘነው ዜና መሰረት ደግሞ ተቃዋሚዎች በመስቀል አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ እንዳያደርጉ ከአዲስ አበባ መስተዳድር መከልከላቸውን መስከረም 12 እና መስከረም 19 ሰማያዊ እና አንድነት ፓርቲዎች በተከታታይ የጠሩዋቸው ሰልፎች በመስቀል አደባባይ እንደማይካሄዱ የአዲስ አበባ መስተዳድር ህዝባዊ ስብሰባ ማስታወቂያ ክፍል አስታውቋል።  
ነገር ግን ሰማያዊ ፓርቲ የፊታችን እሁድ በመስቀል አደባባይ የሚያደርገውን የተቃውሞ ሰልፍ እንደማይለውጥ አስታውቋል። ፓርቲው ነሐሴ 26 የጠራው ሰልፍ በጸጥታ ሀይሎች እንዲደናቀፍ መደረጉ ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment