It encourage all Ethiopians to stand together to overthrow undemocratic regime from motherland Ethiopian.
Saturday, September 21, 2013
አየር ሃይል አደጋ ላይ ነው ተባለ
"ተዋጊ አውሮፕላኖች የኮንትሮባንድ ማመላለሻ ሆነዋል"
የኢትዮጵያ አየር ሃይል እንደገና ካልተዋቀረ አገርን መከላከል የሚችልበት ደረጃ እንደማይገኝ ሻለቃ አክሊሉ መዘነ ለኢሳት አስታወቁ። ተዋጊ አውሮፕላኖች የኮንትሮባንድ ማመላለሻ ሆነው እንደሚአገለግሉ፣ አብራሪ የሚባሉት በሚሊሻ ደረጃ መገኘታቸው፣ የዘር መድልዎ እንደሚደረግ፣ የህወሃት ድጋፍ ያላቸው ብቻ የሚስተናገዱበት መሆኑ፣ ከችግሮቹ በግንባር የሚገለጹ ናቸው።
ላለፉት 15 ዓመታት ያህል በታማኝነት የተጣለባቸውን አደራ መወጣታቸውን የገለጹት ሻለቃ አክሊሉ " የአውር ደንብር" እንዲሉ በአየር ሃይል ውስጥ የሚሰራው የቡድን፣ የዘርና አጠቃላኢ አለው አሰራር ብልሹነት አሳሳቢ በመሆኑ አገር ጥለው በመውጣት ከሶስት ባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን ግንቦት7 ንቅናቄን መቀላቀላቸውን አመልክተዋል።
ሙስና ከጊዜ ወደ ጊዜ መበራከቱንና ከብቁ ስልጠና ይልቅ በፕሮፖጋንዳ ላይ የተመሰረተ የአብራሪ ሚሊሺያ የማዘጋጀት ስራ ላይ ትኩረት መደረጉን ያለመለከቱት ሻለቃ አክሊሉ በአሁኑ ወቅት " ፓይለት የሚባለው ነገር ያከተመለት ነው" ሲሉ ዝነና የነበረው የኢትዮጵያ አየር ሃይል አገር ሊከላከል የሚችልበት አቅም እንደሌለው ተናግረዋል።
80 ከመቶ በላይ መስዋዕትነት በመክፈል አገሪቱን እዚህ ደረጃ ያደረሱት የቀድሞ የአየር ሃይል አባልት መሆናቸውን ያስታወሱት ሻለቃው በርካቶች በምሬት አየር ሃይልን ለመልቀቅ መሰደዳቸውን አመልክተዋል።
የአገሪቱ ብሔራዊ ጥቅምና ህልውና አደጋ ላይ መሆኑንን፣ ወያኔ አገሪቱን ለመበታተን ከመቼውም በላይ እየሰራ እንደሆነና ቀደም ሲል ትንሽም ቢሆን ያሰማቸው የነበረው ይሉኝታ ሙሉ በሙሉ ተሟጦ ማለቁ ከፍተኛ ስጋት እንደፈተረ ሻለቃ አክሊሉ አመልክተዋል። ወደፊት ሰፊ መረጃ እንደሚሰጡ በማመልከት ሃዘናቸውን ገልጸዋል። ኢሳት ያነጋገራቸው ሻለቃ አክሊሉን ጨምሮ በድምሩ 24 የሚጠጉ የአየር ሃይል ባለሙያዎችና ከፍተኛ አብራሪዎች አገር ትለው መክዳታቸው ተጠቁሟል። በቅርቡ አገዛዙን በመለየት ከግንቦት 7 ንቅናቄ ጋር የተቀላቀሉት አራት የአየር ሃይል አብራሪ መኮንኖችና የበረራ አስተማሪዎች ጉዳይ ከፍተኛ መነጋገሪያ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። የግንቦት7 ዋና ጸሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በቅርቡ በርካታ ባለሙያዎች ከተለያዩ የኣለም ክፍሎች አፈር ግጠው፣አፈር ላይ ተኝተውና አፈር በልተው ሳይታገሉ ድል እንደማይገኝ በመረዳት ትግሉን በረሃ በመውጣት እየተቀላቀሉ መሆኑንን መግለጻቸው ይታወሳል። አቶ አንዳርጋቸው ከኢሳት ጋር ባደረጉት ሰፊ ቃለ ምልልስ በቅርቡ ይህ ነው ተብሎ የሚገለጽ ድል እንደሚመዘገብ በርግጠኝነት መናገራቸውም የሚታወስ ነው። የበረራ ባለሙያዎቹ አገር ጥለው ስለመሄዳቸው ከኢህአዴግ ወገን እስካሁን ድረስ ማስተባበያ አልተሰማም።
በኢትዮጵያ አየር ሀይል ውስጥ በአብራሪትና በበረራ አስተማሪነት ሲያገለግሉ ቆይተው ስርአቱን የተለዩት አራቱ የበረራ ባለሙያዎች ካፒቴን አክሊሉ መዘነ፣ ካፒቴን ጥላሁን ቱፋ፣ ካፒቴን ጌቱ ወርቁና ካፒቴን ቢንአም ግዛው መሆናቸውን በድምጽ በመጥቀስ ሻለቃ አክሊሉ ፍትህ የሰፈነባት ኢትዮጵያን ለመመስረት ግንቢት ሰባትን ተቀላቅለናል በማለት ማረጋገጫ ሰጥተዋል።
SOURCE, GOLGUL WEBSITE
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment