በአሁኑ ወቅት በእስር ላይ የምትገኘውን ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙን የሚጠይቁ ሰዎች ቁጥር እና ዝምድና ወይም ቅርበት
የሚወስነው ገደብ የተጣለው፣ የህግ ታሳሪዋ ባሳየችው የሰነ–ስርዓት ማጓደል ሳቢያ የማረሚያ ቤቱ ባለስልጣናት፣ በህጉ
መሰራት ለመውሰድ የተገደዱት እርምጃ ነው ሲሉ የእርምጃውን ትክክለኛነት ይፋ ያደረጉት የመንግስቱ ኮምንኬሽን ጽህፈት
«"ሲፒጄ" የጭፍን ግምት ወሰደ ያሉትን የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ይህን ያደረገበት ብቸኛ አላማም፣
መንግስታቸውን ለመወንጀልና የኢትዮጵያን ገጽ ለማበላሽት
ከተነጣጠረ እላማ የመነጨ ነው» ሲሉ ገልፀዋል።
«የኢትዮጵያ መንግስት እርምጃውን መውሰዱን ማመኑ፣ በራሱ አዎንታዊ እርምጃ የሚቆጠር ነው ያለው» ሲፒጄ በበኩሉ፣
«የመንግስቱ ሃላፊነት የግለሰቦችን የመፃፍ ነፃነት በመገደብ ማን ጋዜጠኛ መሆን እንዳለበትና ማን እንደሌለበት መወሰን ሳይሆን
የዜጎችን ሕገመንግስታዊ መብት ማስከበር ነው» ሲል ተችቷል::
Tom Rode፣ በናይሮቢ የድርጅቱ የምስራቅ የአፍሪካ አማካሪ ናቸው። በመንግስቱ ባለስልጣን የተሰነዘረውን አስተያየት
አልገረመኝም ይላሉ «አባባሉ አሳዛኝ ቢሆንም አልገረመኝም። ሲፒጄ የውስጥ ስራችን ለጋዜጠኞች መብት መቆም እንጂ፣
በኢትዮጵያ መንግስት ስራ የተነጣጠረ ሌላ አላማ የለንም። የኢትዮጵያ መንግስት ማን ጋዜጠኛ እንደሆነ ማን እንዳልሆነ
የመወሰኑ ስልጣን የነሱ ድርሻ ማድረጋቸውን በጣም አስገርሞኛል የኢትዮጵያ መንግስት እንዲህ ያለውን እርምጃ የወሰድኩት
በዚህ ምክንያት ነው ሲል በቅርብ ጊዜያት የሚቀርቡበትን ውንጀላዎች ተቀብሎ እርምጃውን ይፋ ሲያደርግ ያሁኑ
የመጀመርያው መሆኑ ነው።
SOURCE, VOA
No comments:
Post a Comment