Tuesday, December 3, 2013

የወያኔ አገዛዝ በመልዕክተኞቹ በኩል ላቀረበው የ“እንደራደር” ጥያቄ ከግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የተሰጠ ምላሽ


ሰበር ዜና፣ ግንቦት 7 ወያኔ ላቀረበው “እንደራደር” ጥያቄ መልስ ሰጠ
 
ወያኔ ኢትዮጵያ ዉስጥ የገነባዉ ሥርዓት በከፍተኛ ችግሮች የተወጠረ ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የመሪው ሞት በወያኔ መሀል ያስከተለው ቀውስ፤ የሕዝብ ሁለገብ ትግል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎለበት መሄድ የፈጠረበት ስጋት እና ምርጫ በደረሰ ቁጥር የሚደርስበት ጭንቀት መጨመር ተደማምረው ውጥረቱን ወደ ከፍተኛ ደረጃ እያደረሱት መሆኑን የሚያሳዩ በቂ ምልክቶች አሉ። የእስካሁኑ ተሞክሮዓችን እንደሚያሳየው ወያኔ ውጥረት ሲበዛበትና መዉጪያና መግቢያዉ ሲጠፋዉ ፣ ተቃዋሚ ድርጅቶችን “እንወያይ፣ እንደራደር” በማለት ለውጥረት ማስተንፈሻ ጊዜ የሚገዛ መሆኑን ነው። ሰሞኑን በወያኔ አገዛዝ መልዕክተኞች በኩል የደረሰንን “የእንደራደር” ጥያቄ ንቅናቄያችን በዋናነት ያየው ወያኔ እንደለመደው ድርድርን ለውጥረት ማስተንፈሻነት ለመጠቀም እየሞከረ መሆኑን ነው።Ginbot 7 logo
የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚመኘው ዲሞክራሲያዊ ለውጥ በሰላማዊ መንገድ በሚደረግ ትግልና በጠረጴዛ ዙሪያ በሚደረጉ ዉይይቶች ቢመጣ የግንቦት 7 ምርጫ መሆኑን ንቅናቄያችን በተደጋጋሚ ግልጽ አድርጓል። ግንቦት 7ን ሁለገብ ትግል ውስጥ እንዲገባ ያስገደደው የወያኔ እምቢተኝነትና እብሪት ብቻ ነው።
የግንቦት 7 ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የሰሞኑ የወያኔ የእንደራደር መልዕክት እንደደረሰው በጉዳዩ ዙሪያ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ይህ ጉዳይ የኢትዮጵያን ሕዝብ ባጠቃላይ እንጂ ግንቦት 7ን ብቻ የሚመለከት ጉዳይ እንዳልሆነ ከድምዳሜ ላይ ደርሷል። ይህ ጉዳይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ከሚያደርገው ትግልና እየከፈለ ካለው መስዕዋትነት ጋር በቀጥታ ግንኙነት አለው። በመሆኑም፤ ለቀረበልን ጥያቄ ግልጽ መልስና፤ ድርድር ስለሚባለው ጉዳይም ያለንን አቋም ጉዳዩ በቀጥታ ለሚመለከተው የኢትዮጵያ ሕዝብና የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ሁሉ ለማቅረብ የሚያስችል ተጨማሪ አጋጣሚ አድርገን ወስደነዋል። በዚህም መሠረት ለቀረበልን ጥያቄ የሰጠነዉን መልስና አቋማችንን በድርጅታችን ድረ ገጽ ላይና በሌሎች መገናኛ ብዙሀን በኩል በይፋ ለመግለጽ ወስነናል።
በድርድር ስለሚመጣ ለውጥ ያለን የመርህ አመለካከት:
ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ግልጽ እንዳደረግነው ድርጅታችን ከምሥረታው ጀምሮ የትግል ስልቱን ሲወስን እምነቱ አድርጎ የተነሳው ዴሞክራሲያዊ ለውጥ በሀገራችን በሰላማዊ መንገድና በድርድር ቢመጣ በእጅጉ የሚፈልገውና የሚመኘው መሆኑን ነው:: ድርጅታችንን ወደ ሁለንተናዊ ትግል የገፋው በመግቢያው ላይ እንደገለጽነው የወያኔ እብሪት ብቻ ነው:: የቀረበልን ምርጫ በባርነትና በውርደት መኖር ወይም ለነፃነት እየታገልን መሞት ቢሆን ኖሮ ንቅናቄያችን የሚመረጠው ምን ግዜም ለነፃነትና ለአገር አንድነት ታግሎ በክብር መሞት መሆኑን በተደጋጋሚ ለሕዝብ ግልጽ አድርገናል። ይህ የማይናወጥ አቋማችን ደግሞ ለይምሰል የተቀመጠ አቋም ሳይሆን ከልባችን የምናምንበትና ኢትዮጵያን ጨምሮ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ አባላቶቻችንን ያሰባሰብንበት አቋም ነው። ዛሬ በትግሉ ግንባር የምንንቀሳቀሰውና ወደ ግባችን የሚወስደንን ተጨባጭ እርምጃዎች እየወሰድን ያለነውም በዚሁ አቋማችን ዙሪያ ነዉ።
ይህ አቋማችንና እምነታችን በአንድ ላይ ጎን ለጎን የሚሄዱ ሁለት መርሆችን አጣምሮ የያዘ ነዉ። አንደኛው፣ ሂደትን በሚመለከት ሁሌም ለድርድር ክፍት መሆኑን የሚያመለክት ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ፣ ይህ የድርድር ሂደት እንዲያው ለለበጣ የሚደረግ ሳይሆን ወደሚፈለገው ነጻነት በአነስተኛ መስዕዋትነት ሊያደርስ ይችል ከሆነ በሩን ላለመዝጋት እንጂ፣ በምንም አይነት ዋና ውጤቱን፤ ማለትም ኢትዮጵያን እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሀገር ማድረግን፤ የሚቀይር ወይንም ከዚያ ያነሰ ውጤትን ለመቀበል መፍቀድን ፈጽሞ የማያመለክት መሆኑን ነው::
በእኛ በኩል ድርድሩን አስፈላጊና ጠቃሚ የሚያደርጉት መነሻ የፖለቲካ እሳቤዎችም ከእነኝሁ ሁለት መንታ ገጽታዎች የሚመነጩ ናቸው:: በድርድር ለሚገኝ ፍትሀዊና እውነተኛ ውጤት ክፍት መሆናችንን ሁሌም እናሳያለን፤ ነገር ግን ይህን የምናደርገው የሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነት የተረጋገጠባትን ኢትዮጵያን እውን ማድረግ የሚጠይቀውን ማንኛውንም መስዋዕትነት መከፈል አለበት የሚለውን መሠረታዊ የአካሄድ መርህ በመመርኮዝ እንጂ መርሀችንን ለድርድር ለማቅረብ እንዳልሆነ በግልጽ መታወቅ ይኖርበታል::
ስለዚህም:
ሀ)    የድርድሩ ውጤት የኢትዮጵያን ሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነት ያረጋገጠ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን በአስቸኳይ እውን ማድረግ መሆን ይኖርበታል:: ይህ ዋናው ግብ ሆኖ ከዚህ በመለስ የሚኖሩ በሂደት የሚገኙ አነስተኛ ግቦች ሊኖሩ ይችላሉ (ለምሳሌ የፖለቲካ እስረኞች ማስፈታት…ወዘተ):: ሆኖም በምንም አይነት ለእነኝህ መለስተኛ ግቦች ተብሎ ዋናውን ግብ የሚያሳጣ ወይንም ጊዜውን ያላግባብ የሚያስረዝም ድርድር፣ ድርድር ነው ብሎ ድርጅታችን አይቀበልም። ስለዚህም ዋናው የድርጅታችን ዓላማና ግብ የሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነት ፣ በፍጹም ለድርድር የሚቀርብ ጉዳይ አይደለም:: በሥልጣን ላይ ባለው ኃይል በኩል ወደዚህ ግብ ለመድረስ ቁርጠኝነቱ በሌለበት ሁኔታ በሚደረግ ማንኛውም አይነት ድርድር ውስጥ ግንቦት 7 አይሳተፍም::
ለ)  በግንቦት 7 እምነት ማንኛውም ድርድር ወያኔ ከግንቦት 7 ጋር በተናጠል የሚያደረገው ሳይሆን ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ሁሉንም የፖለቲካ ኃይሎች ያካተተ መሆን ይኖርበታል:: ድርጅቶችን በተናጠል እየለያዩ “እንደራደር” ማለት በራሱ ጊዜያዊ የፖለቲካ ጥቅም ስሌትን የያዘ እሳቤ እንጂ፣ በዘላቂነት አገሪቱን እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ አገር ለማድረግ መፈለግን አያመለክትም:: ለአንድ ድርጅት ለብቻው የሚመጣ ወይም የሚጠቅም ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የለም:: ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የመፍጠር ፍላጎት ያለው ድርድር በአገሪቱ ያሉትን የተለያዩ የፖለቲካም ሆነ የሲቪክ ኃይሎችን ያካተተና ያመኑበት መሆን ይኖርበታል:: የሚደረገው ድርድርም ማን በስልጣን ላይ ይውጣ ወይንም የፖለቲካ ስልጣንን ባሉት ኃይሎች መሀከል እንዴት እናከፋፍለው የሚል የስልጣን ቅርምት ድርድር ሳይሆን፤ ሕጋዊና የሕዝቡን የሥልጣን ሉዓላዊነት ባረጋገጠ ሁኔታ የፖለቲካ ስልጣን እንዴት እንደሚያዝ ፍትሀዊ የሆነ ሂደትን ለማስጀመር የሚደረግ ድርድር መሆን አለበት::
ሐ) ቀደም ብለን እንደጠቀስነው ይህ ጉዳይ የሚመለከተው አንድን ድርጅት ወይንም የፖለቲካ ድርጅቶችን ብቻ ሳይሆን መላውን የኢትዮጵያን ሕዝብ ነው:: ይህ እስከሆነ ድረስ እንዲህ አይነት ድርድር ከሕዝቡ በተደበቀ ሁኔታ በሚስጥር የሚካሄድበት ምንም ምክንያት የለም::
2)   ከዚህ በፊት ከወያኔ ጋር ከተደረጉ ድርድሮች ያገኘናቸው ተመክሮዎችና ከዚህ በመነሳት ወደፊት በሚደረጉ ምንም አይነት ድርድሮች እንዳይደገሙ ለመጠበቂያ የሚሆኑ ከአሁኑ መወሰድ ያለባቸው እርምጃዎች
ከማንኛውም ወገን ጋር የሚደረግ ድርድር የተደራዳሪዎቹ ምንነት፤ ውስጣዊ ባህርያቸውን፤ ከተለምዶ ተግባራቸው ያላቸውን ተአማኒነትና ወደዚህኛው ድርድር ያመጣቸውን ምክንያቶች በበቂ ከመገንዘብ ጋር ተያይዞ የሚታይ ጉዳይ ነው:: ቃሉን አክባሪና ተዓማኒ ከሆነ ሰው ጋር የሚደረግ ድርድርና ያለፈው ታሪኩ ምንም አይነት የተዓማኒነት ባህርይ ከማያሳይ ቡድን ጋር የሚደረግ ድርድርም ሆነ ለድርድሩ የሚደረግ ዝግጅት ለየቅል ናቸው:: ይህ ማለት ግን ተዓማኒነት ካለው ኃይል ጋር ብቻ ነው ድርድር የሚካሄደው ማለት አይደለም:: በፍጹም ተዓማኒ ካልሆነ ኃይል ጋር የሚደረግ ማንኛውም ድርድር ግን ድርድሩ በእርግጥም ተግባራዊ ሊሆን የሚችል መሆኑን የሚያሳዩ ጠንካራ መጠበቂያዎች (System of Verification) እንዲሁም ግልጽ የመተግበሪያ ሥርዓቶች (Implementation Mechanism) ሲደረጉለት ብቻ ነው ከምር ሊወሰድ የሚችለው:: ከዚህም ባሻገር ግን መጀመሪያውኑ ወደ ድርድር የሚመጣው ለጊዜያዊ የፖለቲካ ጥቅም ሳይሆን በእዉነተኛ መንፈስ ከድርድር የሚመጣውን ውጤት በመፈለግ መሆኑን የሚያሳዩ “የመተማመኛ” ምልክቶች ሲያሳይ ነው በእርግጥም ወደ ድርድር የመጣው ከልቡ ድርድሩንና ከድርድሩ የሚመጣዉን ዉጤት ፈልጎ መሆኑን ለማመን የሚያስችለው::
ወያኔ ከተቀናቃኝ ወገኖች ጋር “ድርድር” ሲያደርግ የመጀመሪያ ጊዜዉ አይደለም:: እኛ እስከምናውቀው ድረስ ምናልባት በኃይል ይበልጡኛል ብሎ ከሚያምናቸው ወገኖች ጋር ካልሆነ በስተቀር፣ በረሃ ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ በማንኛውም ጊዜ ለቃሉ ታማኝ፤ ለመርሁ እውነተኛ፤ ለደረሰበት ስምምነት ተገዢ ሆኖ አያውቅም:: ይልቁንም ሶስተኛ አደራዳሪ ወገኖችን በሚያሸማቅቅና በሚያሳፍር መልኩ ውሸትን እንደ አዋቂነት፤ ማጭበርበርን እንደ ብልጠት፤ የተስማማበትን በገሀድ ማፍረስን እንደ የአመራር ብልሀት አድርጎ የሚያይ፤ ምንም እፍረትና ጨዋነት የሚባል ነገር ያልፈጠረበት እኩይ ኃይል ነው:: ከራሱ የድርጅት ጥቅምና በስልጣን ከሚገኝ የዝርፊያ ሀብት ማካበት ባሻገር፤ ለአገር ዘላቂ ጥቅም ብሎ የራሱን ጥቅም አሳልፎ የሚወስደው ምንም እርምጃ እንደሌለ በተግባር በተደጋጋሚ ያረጋገጠልን ኃይል ነው:: በግንቦት 7 ውስጥ ያለን ወገኖች ይህንን የወያኔ ባህርይ በንድፈ ሀሳብ ደረጃ ሌሎች ጽፈውት ያነበብነው ሳይሆን፣ እራሳችን በተግባር በተሳትፈንበት ሂደት ያገኘነው ጥልቅ ግንዛቤ ነው:: ይህንን ደግሞ በአንድ አጋጣሚ ብቻ ሳይሆን ከድርጅቱ ታሪክ ጋር የተጣበቀ፤ በአመራር አባላቱ ላይ እንደ ግል ባህርይ የሰረጸ መሆኑን እስክንገነዘብ ድረስ በተደጋጋሚ የተመለከትነው ነው:: ስለዚህም ከዚህ ኃይል በኩል የሚመጣን የ “እንደራደር” ጥያቄ ከዚህ በፊት እንዳደረገው ለገባበት የፖለቲካ ውጥረት ማስተንፈሻ፣ ለውሸት ፕሮፓጋንዳው መጠቀሚያ፤ ለጊዜያዊ የፖለቲካ ትርፍ መሰብሰቢያ፤ የዴሞክራሲ ታጋዮችን ትጥቅ ማስፈቺያና ወኔ መስለቢያ አድርጎ እንዲጠቀምበት በፍጹም አንፈቅድለትም:: ስለዚህም ከላይ በመርህ ደረጃ ከጠቀስናቸው ሶስት ጉዳዮች በተጨማሪ ምንም ዓይነት ድርድር ከመደረጉ በፊት ወያኔ ጉዳዩን ከምር የወሰደው መሆኑን የሚያሳዩ “የመተማመኛ” እርምጃዎች መውሰድ አለበት ብለን እናምናለን::
እነኝህም፣
ሀ)  ሁሉንም የፖለቲካ እስረኞች፤ ጋዜጠኞች፤ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መፍታት:: ይህ ደግሞ በግልጽ     የሚታወቁ እስረኞችን ብቻ ሳይሆን በድብቅ የተቋቋሙ ማጎሪያና ማሰቃያ ቤቶች ያሉትን ሁሉ ማጠቃለል አለበት።
ለ)  በሕዝብ በተለይ በተቃዎሚ ኃይሎች ላይ ወያኔ በየቀኑ እያካሄደ ያለውን ወከባና እንግልት ባስቸኳይ ማቆም፣ ሰብዓዊና የዜግነት መብታቸውን ማክበር አለበት።
ሐ)   በፖለቲካ ምክንያት ከዚህ በፊት የተወሰዱ ሁሉም ዓይነት ፍርድ ተብዮ ውሳኔዎች እንዲሻሩ ማድረግ፤ በሂደት ላይ ያሉ ከፖለቲካ ጋር የተያያዙ ምንም አይነት ክሶችን ማቋረጥ አለበት።
መ)   ሕዝብን በፍርሃትና በስጋት ለማቆየት ሆነ ተብለው የወጡ አፋኝ ህጎችን በአስቸኳይ ማንሳት አለበት።
ሠ)   ማንኛውም ድርድር ገለልተኛ የሆኑ ሶስተኛ ወገኖች ባሉበት፤ የድርድሩ ሂደት በምስልና በድምጽ ተቀርጾ በገለልተኛ ወገኖች እጅ ብቻ የሚቀመጥ፣ የድርድሩ ቦታም የተደራዳሪ ወገኖች በጋራ በሚስማሙበት ቦታ መሆኑን መቀበልና ይህንንም በግልጽ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ማሳወቅ አለበት።
እነኝህ ከላይ ያስቀመጥናቸው በወያኔ በኩል የሚወሰዱ “የመተማመኛ” እርምጃዎች ለተቃዋሚዎች ተብሎ የሚወሰዱ እርምጃዎች አይደሉም:: ወያኔ እነዚህን እርምጃዎች ለመውሰድ ቁርጠኝነት ሳይኖረው ለእውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መመስረት የሚደረግ ድርድር ላይ ከምር ይሳተፋል ብለን ማመን በፍጹም ስለማንችል ነው ::
እስከዚያው ድረስ ግን ግንቦት 7ም ሆነ ሌሎች ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መመስረት በቁርጠኝነት የምንታገል ኃይሎች፣ ወያኔ እነኝህን የመተማመኛ እርምጃዎች እስኪወስድና ቀደም ብለው በተቀመጡት መርሆች መሠረት በሚደረግ ድርድር በተግባር ሊመነዘር የሚችል ስምምነት፣ አልፎም ለምንም አይነት ማጭበርበርና መንሸራተት እድል የማይሰጥ ጠንካራ መጠበቂያዎች መኖራቸው እስኪረጋገጥ ድረስ፣ የጀመርነውን ትግል ይበልጥ አጠናክረን የምንገፋበት እንጂ በምንም አይነት ለአንድ አፍታም ቢሆን በድርድር ስም የማንዘናጋ መሆኑን አበክረን እናስታውቃለን::
የግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ፣
ኅዳር 23፣ 2006 ዓ:ም

Saturday, November 30, 2013

ከኢትዮጵያ ዜጎች ጋር በተያያዘ በሳውድ አረቢያ ከፍተኛ የሆነ አደጋ ማንዣበቡን ኢትዮጵያውያን ተናገሩ



ኢሳት ዜና :-በሳውድ አረቢያ የሚታየው ሁኔታ እጅግ አስፈሪ ነው ይላሉ ያነጋገርናቸው ዜጎች። ከ40 ሺ በላይ ኢትዮጵያን በእስር ቤቶች ውስጥ ይገኛሉ። ወደ አገራቸው ለመመለስ የሚፈልጉ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ቀናቸውን ይጠባባቃሉ። የኢትዮጵያ መንግስት በመቶ ሺ የሚቆጠረውን ስደተኛ ለማስተናገድ የመደበው የሰው ሀይል 40 ብቻ ነው። የሳውድ አረቢያ መንግስት ደግሞ በተዘዋዋሪ መንገድ ኢትዮጵያውያን ከአገሪቱ ምድር ተጠራርገው እንዲወጡ እየቀሰቀሰ ነው። ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ፣ በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ አደጋ ሊፈጠር ይችላል ብሏል  አንድ ስሙ እንዳይገለጽ የፈለገ ጋዜጠኛ።
በዛሬው እለት በተለያዩ የሳውዲ ከተሞች የተበተነው የኤስ ኤም ኤስ መልዕክት  ህጋዊ ለተባሉትም ሆነ ህገወጥ ለሚባሉት ኢትዮጵያውያን የማስጠንቀቂያ ደወል ነው ይላሉ እኝህ ጋዜጠኛ።



በሞባይል ስልኮች የተበተነው ኤስ ኤም ኤስ ኢትዮጵያውያንን ቀጥራችሁ የምታሰሩ እንዲሁም መኖሪያ ቤት ያከራያችሁ ሁሉ በአስቸኳይ እንድታስወጡ፣ ይህን ባታደርጉ ግን 100 ሺ ረያል ትከፍላለችሁ የሚል እንደሆነ ያነጋገርናቸው ኢትዮጵያውያን ገልጸዋል። ይህን መልእክት ተከትሎ በርካታ ኢትዮጵያውያን ከተከራዩበት ቤት ተባረዋል። 9 ኢትዮጵያውያንን ወደ አስጠጋው ኢትዮጵያዊ በመደወል መታሰቢያ ቀጸላ አነጋግራቸዋለች። እርሱ እንደሚለው መልክቱ መተላለፉን ተከትሎ ጓደኞቹ ከቤታቸው እንዲወጡ ተደርጎ በእርሱ ቤት ተጠልለዋል::
ከቤታቸው ከተባረሩት መካከል አንዱ ከ8 ወራት በፊት አባቱ ቤታቸውን ሸጠው ፣ በኪራይ ቤት እየኖሩ በህጋዊ መንገድ እንደላኩት ይናገራል። አሁን ቤትክን ለቀህ ውጣ ተብሎ ህይወቱ አደጋ ላይ ወድቋል:: 

የሳውዲ መንግስት በኦፊሴል እንዲህ አይነት መልክት ያስተላልፍ እንደሆነ የጠየቅነው ጋዜጠኛ፣ መንግስት በቀጥታ እንዲህ አያደርግም ነገር ግን እርሱ ባሰማራቸው ሰዎች አማካኝነት መልክቶችን እንደሚሰድ ይታወቃል ብሎአል።
የኢትዮጵያ መንግስት ጠንካራ የዲፕሎማሲ ዘመቻ በማድረግ በመቶሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ህይወት መታደግ ሲችል በቀን ይህን ያክል ሰው አስመጣሁ በማለት ፕሮፓጋንዳ ይነዛል የሚለው ጋዜጠኛው፣ በሳውዲ የቀረው ኢትዮጵያዊ ወደ አገር ቤት የተመለሰውን በብዙ እጥፍ ይበልጣል ሲል በአገሪቱ ያለውን እውነታ አስረድቷል።
በሌላ በኩል ከሳውድ አረቢያ ወደ የመን የገቡ 3 ሺ ያክል ኢትዮጵያውያን በምግብ እጥረት ተጎሳቁለው እንደሚገኙ እስር ቤት ድረስ በመሄድ ጋዜጠኛ ግሩም ተክለሀይማኖት ጎብኝቷቸዋል።

Wednesday, November 27, 2013

EU Member of Parliament Ana Gomes in Addis Ababa November


Ana Gomes, known for publicly criticising Ethiopia following the 2005 government crackdown
Serious talk! EU Member of Parliament Ana Gomes, known for publicly criticising Ethiopia following the 2005 government crackdown, which claimed over 200 lives, in a seemingly serious discussion during lunch break with Ethiopian MP and Speaker of the House Abadulla Gemeda in Addis Ababa, November 25, 2013. ANDUALEM SISAY | NATION MEDIA GROUP
The 26th European Union (EU) and African Caribbean Pacific (ACP) Joint Parliamentary Assembly (JPA) opened in Addis Ababa, Ethiopia Monday morning.
The assembly is expected to debate several issues, ranging from use of natural resources to fiscal reform and redistribution of wealth and decentralised cooperation.
The gathering is also expected to discuss respect for the rule of law and the role of an impartial and independent judiciary and South-South and triangular cooperation.
The assembly that will be concluded on Wednesday, has no decision-making powers.
However, it allows elected representatives of ACP countries to address their concerns directly to the EU Commission and be updated on the negotiations on trade deal, such as the Cotonou Agreement.
“There is an ample room for more enhanced partnership in many areas of interest to both sides,” said Ethiopian Prime Minister Hailemariam Desalegn, while opening the assembly.
“But in a large sense, this relationship should not in any way be based on the rather obsolete assumption that one side is the ultimate provider and the other perennial receiver of resources whatever the object of the relationship might be – economic or political.”
JPA comprises 78 members of parliament and 12 vice-presidents from both sides (EU and ACP).
The assembly is expected to be concluded after discussing social and environmental impacts of pastoralism on ACP countries on the last day.
JPA meets twice a year, once in the EU, traditionally in the country holding the presidency of the Council of the EU and once in an ACP country, determined by the group of ACP countries.

Source: AFRICA REVIEW

ሰማያዊ ፓርቲ አፄ ምኒልክ የሞቱበትን አንድ መቶኛ ዓመት በዓል ያከብራል

 
 
 
 
 
 ሰማያዊ ፓርቲ አፄ ምኒልክ የሞቱበትን አንድ መቶኛ ዓመት በዓል እንደሚያከብር የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት አስታውቋል። አፄ ምኒልክ የሞቱበት ዕለት ታህሳስ 3 ቀን በመሆኑ ዕለቱን የፓናል ውይይት፣ ጉብኝትና ኤግዚቪሽኖች በማዘጋጀት በአሉን በልዩ ልዩ ፕሮግራሞች ለማክበር እየተዘጋጁ መሆኑን አስታውቋል።

በዕለቱ በተመሳሳይ ቀን ያለፉት ፊታውራሪ ኃብተጊዮርጊስ ዲነግዴ አብረው የሚታሰቡ መሆኑን የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወጣት ብርሃኑ ተ/ያሬድ አስታውቋል። ፓርቲው ወደፊትም “የታላቋ ኢትዮጵያ ቀን” በሚል በየሶስት ወሩ ቋሚ ፕሮግራም እንደሚያዘጋጅ ጨምሮ አስታውቋል። አፄ ምኒልክ እና ፊታውራሪ ኃብተጊዮርጊስ ዲነግዴ የሚዘከሩበት ቀን የዚሁ የታላቋ ኢትዮጵያ ቋሚ ፕሮግራም አካል መሆኑንም አመልክቷል።

አፄ ምኒልክንም ሆኑ ፊታውራሪ ኃብተጊዮርጊስ ዲነግዴን መዘከር ያስፈለገው የሀገሪቱን አንድነት ጠብቀው ከማቆየት ባሻገር በሀገሪቱ ዘመናዊነት፣ ቴክኖሎጂ መስፋፋትና እድገት ፈርቀዳጅ በመሆናቸው እንዲሁም በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቁሮች በነጮች ላይ ድል እንዲጎናፀፍ ያደረጉ ገናና መሪዎች በመሆናቸው ነው ብሏል።


Monday, November 25, 2013

ግድ የለሹ መንግስት ተብዬው! ከሀና ሰመረ (ኖርዌይ)


የምንሰማውና የምናየው የኛው ከልክ ያለፈ አሳዛኝ ዜና አላስችል ቢለኝ እንደው ትንሽ የውስጤን ሀዘን እና ብሶቴን ቢገልፅልኝ ብዬ ብዕሬን አነሳው::

እኔ የምላቹ እንደው የሰው ልጅ እንዲህ እንዴት ከፋ? አምላክ በራሱ አምሳል የፈጠረውን ሰውን የሚያህል ክቡር ፍጡር ለማጥፋት እንዲህ መሯሯጥ ምን የሚሉት ነው? እኛ ኢትዮጵያኖች ለምን ይሆን እንዲህ በየቦታው ስቃያችን የበዛው? እውነት ግን የምላችሁ ወገኖቼ አያት ቅድመ አያቶቻችን አገራችንን ከወራሪ ጠላት ጠብቀው ያስከበሩ እና እንዳስከበሩ ሲነገር የቆየው የጀብዱነት ታሪክ በደመ ነፍስ በሚወዛወዘው በወያኔ ድርጅት ከስር መሰረቱ ለማፍረስ የታለመ ነው:: ይህንን እኩይ ተግባር በቸልተኝነት መመልከት ከታሪክ አጥፊው ጎራ አብሮ ከመሰለፍ ተለይቶ አይታይም:: ግን እስከመቼ ብለን የጊዜ ቀጠሮ ይዘን ነው አያቶቻችን ደምና አጥንት ከፍለው ባስረከቡን ሀገር ላይ ነፃነታችንን ተነፍገን ተራ እየጠበቅን የስደትን መራራ ፅዋ የምንጎነጨው ግን እስከመቼ? ይህንን ጥያቄዬን ልብ ያለው ለራሱ ይመልስ::

ኢህአዴጋውያንን ሳይሆን በመላው አለም ያሉ ኢትዮጵያውያንን በሙሉ ያሳዘነና ያስቆጣው በሳውዲ አረቢያ የሚኖሩ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ላይ የሚደርሰውን በርካቶችን እስከ ሞት ፤ ሴት እህቶቻችንን እስከ መደፈር ፡ እንዲሁም ወንድሞቻችንን ለከፍተኛ ድብደባ ከዳረገውም በላይ የህወሀት አባላት በሳውዲ አረቢያ ልጅም ዘመድም ስለሌላቸው ወገኖቻችንን ካሉበት ችግር ለማውጣት የተከፈለ አመርቂ እንቅስቃሴ የለም:: እንዲያውም በተገላቢጦሽ አረቦቹ በመለስ ዜናዊ ለ60 ዓመት ሊዝ የሰጣቸውን መቶ ሺህ ሄክታር የኢትዮጵያውያኑ መሬት ላይ ህይወታቸውን ላጠፉ ፤ ሰብዓዊ መብታቸውን ለገፈፉ ፡ እንዲሁም ደማቸውን ላፈሰሱት ለሳውዲ አረቢያ ህዝብ ቀለብ ሩዝ እያመረቱ ነው::

ይህም አልበቃ ብሎ ኢትዮጵያኖች ፍትህን ፍለጋ በተሰደዱበት ዓለም ሁሉ በሙሉ ነፃነት የወገኖቻቸውን በደል እልህ በተሞላበት ተቃውሞ ሲያሰሙ ፤ ህዳር 6 ቀን 2006 ዓ.ም ከጠዋቱ 5:00 ሰዓት በተለምዶ ወሎ ሰፈር ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ ከአይቤክስ ሆቴል ፊት ለፊት በሚገኘው የሳውዲ አረቢያ ኤምባሲ ደጃፍ ላይ የተቃውሞ ድምፃቸውን ሊያሰሙ የተሰበሰቡትን በተወለዱበት እና በገዛ ሃገራቸው የወገኖቻቸውን ስቃይ እንዳይቃወሙ በፖሊስ የመባረርና ከፊሉም ለእስር ተዳርጓል::

ግን ማን ይሆን ስደትን ሐሴት አድርጎ ቀዬውን ጥሎ በባዕድ ሀገር የሚንከራተት? ፍትህ ቢጓደልበት፤የብልሹ አስተዳደር ግፍና የጭቆና ቀንበር ከአቅሙ በላይ ቢሆንበት እንጂ፤ ለዚህ ሁሉ ችግሮች ተጠያቂው ለዜጎቹ ህልውናና ክብር ግድ የለሽ የሆነው መንግስት ተብዬው ነው:: ለነገሩ ወያኔ ብዙ ትንንሽ አድርጎ ከፋፍሎ የወሰነውን እኛ ካላፈራረስነው ችግራችንም ማብቂያ አይኖረውም የወያኔም አላማ ግብ ይመታለታል ስለዚህ ወገኖቼ “ህዝብ መንግስትን ሳይሆን መንግስት ህዝብን” አገልጋይ የሚሆንበትን ስርዓት ለመገንባት እንዲሁም ለዚህ ያበቃንን ስርዓት ለማስወገድ ድክመታችንን በጋራ መፍታት የትግሉ ቅድመ ሁኔታ መሆን አለበት::

ኧረ ማንን ይሆን እንክርዳዱን ከስንዴው አንጓሎ እንዲያስወግድልን የምንጠብቀው?


ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

Such inhuman and shameful treatment of Ethiopian migrants living in Saudi Arabia and other Gulf States should be stopped immediately. by Garbis Korajian

 
I am a fourth generation Ethiopian-Armenian and, like many Armenians who lived in Ethiopia, my grandparents took refuge in Ethiopia after the Armenian Genocide. Those Armenians who were fortunate enough to have escaped the Turkish atrocities and mass murders of the early 20th century repatriated to different countries around the world. Ethiopia was a country that provided unconditional support and welcomed Armenians with open arms. We lived and prospered in Ethiopia where we maintained our institutions such as our churches, schools and community centers without any interference from the Government of Ethiopia and its citizens. We were treated as brothers and sisters and lived a good life. Although I now live in Canada, I still have a lot of love for Ethiopia and the people.
Therefore, I find it necessary to say a few words about the current mistreatment of Ethiopians in the Gulf States including Saudi Arabia which has been the focus of despicable mistreatment of Ethiopians. For various reasons, mostly economic, today’s young Ethiopians are traveling abroad looking for better opportunities of life through employment. For women, this is mostly domestic help and for men, it would be construction or any other job they can find. Needless to say, life for Ethiopians looking for work and to survive in these countries is not easy. On top of these hardships, the Ethiopians who are law abiding and hard working members of society are facing persecution beyond anyone’s imagination. There is no justification for such cruel behavior.
It is important to remember that one day, the citizens and its descendants from the countries that are committing such atrocities on helpless Ethiopians may very well seek refuge in Ethiopia as was done 1500 years ago. As always, what goes around always comes around. Do not forget your history vis-a-vis Ethiopia and stop mistreating our Ethiopian brothers and sisters living in your country. Start treating them with decency and respect.
 
SOURCE, ABUGIDA