Wednesday, November 27, 2013

ሰማያዊ ፓርቲ አፄ ምኒልክ የሞቱበትን አንድ መቶኛ ዓመት በዓል ያከብራል

 
 
 
 
 
 ሰማያዊ ፓርቲ አፄ ምኒልክ የሞቱበትን አንድ መቶኛ ዓመት በዓል እንደሚያከብር የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት አስታውቋል። አፄ ምኒልክ የሞቱበት ዕለት ታህሳስ 3 ቀን በመሆኑ ዕለቱን የፓናል ውይይት፣ ጉብኝትና ኤግዚቪሽኖች በማዘጋጀት በአሉን በልዩ ልዩ ፕሮግራሞች ለማክበር እየተዘጋጁ መሆኑን አስታውቋል።

በዕለቱ በተመሳሳይ ቀን ያለፉት ፊታውራሪ ኃብተጊዮርጊስ ዲነግዴ አብረው የሚታሰቡ መሆኑን የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወጣት ብርሃኑ ተ/ያሬድ አስታውቋል። ፓርቲው ወደፊትም “የታላቋ ኢትዮጵያ ቀን” በሚል በየሶስት ወሩ ቋሚ ፕሮግራም እንደሚያዘጋጅ ጨምሮ አስታውቋል። አፄ ምኒልክ እና ፊታውራሪ ኃብተጊዮርጊስ ዲነግዴ የሚዘከሩበት ቀን የዚሁ የታላቋ ኢትዮጵያ ቋሚ ፕሮግራም አካል መሆኑንም አመልክቷል።

አፄ ምኒልክንም ሆኑ ፊታውራሪ ኃብተጊዮርጊስ ዲነግዴን መዘከር ያስፈለገው የሀገሪቱን አንድነት ጠብቀው ከማቆየት ባሻገር በሀገሪቱ ዘመናዊነት፣ ቴክኖሎጂ መስፋፋትና እድገት ፈርቀዳጅ በመሆናቸው እንዲሁም በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቁሮች በነጮች ላይ ድል እንዲጎናፀፍ ያደረጉ ገናና መሪዎች በመሆናቸው ነው ብሏል።


No comments:

Post a Comment