የፀረ ሙስና ኮሚሽን መረጃ በአንድ መስሪያ ቤት ውስጥ የተካሄደን የሙስና ምዝበራ በሪፖርቱ መጠቀስ ያለበትን ሳይጠቀስ ማለፉ አግራሞትን አጭሮብኛል። ነገሩ እንዲህ ነው ለረጅም አመት በመድሀኒት ዘርፍ የኢትዮጵያ መድሀኒትና የህክምና መገልገያ እቃዎች በማስመጣት ለመላው ሀገሪቱ በማከፋፈል (ፋ.ር.ሚ.ድ) በመባል የሚታወቀው ድርጅት ጉለሌ ጳውሎስ ሆስፒታል ፊት ለፊት የሚገኝ መስሪያ ቤት ሲሆን በሀገሪቱ በሁሉም ሊባል በሚችል ደረጃ ቅርንጫፎች ያሉትና በጣም ጥሩ አገልግሎት ለህብረተሰቡ የሚሰጥ ተወዳዳሪ የሌለው መስሪያ ቤት ነበር።
ሆኖም ህወሀት መራሹ መንግስት ሀገሪቱን ከተቆጣጠረ በኋላ ጥሩ በሚባል መልኩ ስራውን ሲሰራ የቆየ ቢሆንም በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር በ2001 የመስሪያ ቤቱ ስም እንዲቀየርና ተጠሪነቱ በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ስር ሆኖ የሀገሪቱ የእርዳታም ሆነ በግዢ ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት ለተለያዪ ለጤና ተቋማት መድሀኒትና የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች በማቅረብ ስሙም የመድሀኒት አቅርቦትና ፈንድ ኤጀንሲ (መ.አ.ፈ.ኤ) ሆኖ ከዚህ ቀደመም የመንግስት የልማት ድርጅት ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ግን ሙሉ በሙሉ ወደ መንግስት ድርጅት እንዲቀየር ተደርጓል።
የዚህ ጽሁፍ አላማ የመስሪያ ቤቱ አወቃቀርና ስለሚሰጠው አገልግሎት ለማስቃኘት ሳይሆን በመድሀኒት አቅርቦትና ፈንድ ኤጀንሲ ተቋም ውስጥ የተፈጸመን የሙስና ተግባር የጸረ ሙስና ኮሚሽን ሪፖርት መንግስታዊ የሆኑ ድርጅቶች በተለያየ ምክንያት መመዝበራቸውን ሪፖርቱ አንድን ብቻ የሀዋሳ ቅርንጫፍ የመ.አ.ፈ.ኤ በእምነት ማጉደል ወንጀል ግምቱ ብር 1 ሚሊየን 7 መቶ ሺ የሆነ መድሀኒት ተመዝብሮ ለግል ጥቅም መዋሉ በሪፖርቱ ገልጿል።
ሆኖም ይህ የጸረ ሙስና ኮሚሽን መረጃ የሀዋሳን ቅርንጫፍ ነጥሎ ቢጠቅስም ነገር ግን በሀላፊነት የተጠየቀ አለመኖሩ እራሱ አነጋጋሪ ነው። የሚገርመው ደግሞ የአዲስ አበባው ዋናው መስሪያ ቤት እና የጅማው ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት በባሰ ሁናቴ መመዝበሩ የተለያዩ መረጃዎች ስላሉኝ ቀጥሎ በዝርዝር እሄድበታለው።
የዚህ የሙስና ተግባር ባለቤቶች በመጀመሪያ ፋ.ር.ሚ.ድን ወደ መ.አ..ፈ.ኤ ለመቀየር ከመብቃቱ በፊት በሁሉም ክልል ያሉት የመድሀኒት ማስቀመጫ መጋዘኖች በጣም በጥሩ ሁናቴ የተያዙ እንዲሁም በሚገባ ጥበቃ እንደሚደረግላቸው እኔው እራሴ ምስክር ነኝ ምክንያቱም በአንድ ወቅት እዚሁ መስሪያ ቤት ውስጥ እሰራ ነበር።
ሆኖም ይህ ዘረፋ በሶስቱም መስሪያ ቤት የተካሄደ ቢሆንም የሀዋሳውን ብቻ ጸረ ሙስና ኮሚሽን በሪፖርቱ መጥቀሱ የሚገርም ነው። ምክንያቱም አንድ አይነት በሚመስል ሁኔታና በተቀነባበረ መልኩ በዋናው መስሪያ ቤት አዲስ አበባ በሚገኘው እና በቅርንጫፍ ጅማና ሀዋሳ ዘረፋ ተካሂዶባቸዋል።
Via: Zehabesha
No comments:
Post a Comment