Friday, September 13, 2013

አንድነት ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፉን ለመስከረም 19 ቀን 2006 ዓም አራዘመ

መስከረም ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፓርቲው የምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ዘካርያስ የማነብርሀን እንደገለጹት የአዲስ አበባ መስተዳድር ከተማሪዎች ትምህርት መጀመር እና ከተለያዩ የአዲስ አመት በአላት ጋር በማያያዝ ፓርቲው ሰልፉን በሁለት ሳምንት እንዲያራዝም በተጠየቀው መሰረት፣ ጥያቄውን ተቀብሎ ለማራዘም ፈቃደኛ ሆኗል። መስተዳድሩ ፓርቲው ተቃውሞውን መስከረም 19 ማካሄድ የሚችል መሆኑን ከመስተዳድሩ ወረቀት አግኝቷል።

አቶ ዘካሪያስ መስተዳድሩ ሰላማዊ ሰልፉን ለማራዘም የህግ ድጋፍ እንዳለው ገልጸው፣ መራዘሙ ሰፊ ዝግጅቶችን ለመስጠት እድል የሰጣቸው በመሆኑ መቀበላቸውን ገልጸዋል
አቶ ዘካሪያስ መስከረም 19 የሚደረገው የተቃውሞ ሰልፍ የተሳካ እንዲሆን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊረባረብ ይገባዋል ብለዋል።
ሰማያዊ ፓርቲም እንዲሁ መስከረም 12 ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እቅድ ማውጣቱ ይታወቃል። ሰማያዊ ፓርቲ የጠየቀውን ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ፈቃድ ካገኘ ፣ በአዲስ አበባ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ 2 የተቃውሞ ሰልፎች ይካሄዳሉ ማለት ነው።
SOURCE, ESAT

No comments:

Post a Comment