Saturday, February 22, 2014


Human Trafficking in Ethiopia
 
Ethiopia is known to be one of the top countries for facing human trafficking these days. According to global slavery index report in 2013  in recent years Ethiopia has seen a rapid increase in outward migration, with millions of Ethiopians travelling throughout Africa and overseas, mostly to Gulf States and the Middle East, to find work. Every year, 80,0000 Ethiopians make journey to Saudi Arabia through Yemen. Government body which is facilitating this phenomena is The Ethiopian Ministry of Labor and Social Affairs, . It is reported that it reviewed and approved 198, 000 contracts for overseas employment, predominately for domestic workers in 2012. Irregular migration, including migration facilitated by illegal brokers, makes up 60 – 70%. In addition to this, The journey they have to pass through is not safe and includes a lot of suffering. many Ethiopia migrants are subjected to suffering, injury, rape and death during their journey.  Many will be hijacked and requested for money or else they will be killed and their organs will be sold illegally. However, still this day many chose to pass through his dangerous journey willing to risk their life. But why?

There are a lot of reasons for resulting and facilitating migration of citizens of Ethiopia. However, one way or another each cause or reason revolves around the action of the government in power and its supporters. For the past 23 years Ethiopia is ruled by this dictatorship, where freedom of speech, political freedom, equality, justice has been anything but way far from the people. Whereas, corruption,  jailing & killing innocent people, stilling peoples vote during election, forced eviction from ones own land and many more has been very common to be observed in the society. We see government officials sitting and running offices which is beyond their skill and education just because they are member of TPLF. Due to this and many other constraints, dreams of  educated and potential  youth is being shattered everyday.

Unfortunately, it became very hard to overthrow current government peacefully and by force. The results of the past four election taking place during this past 23 years show that the government is not willing to negotiate power peacefully. To make things worse on the last elections result, the government clearly showed that there are no room for sayings of political opposition parties opinion by making sure all the seats except one being taken by TPLF. Everyone can clearly see that how shallow the strategy of the government is for improvements.

In addition to that, money donated by the western world and world bank in the name of children and women, food security, education,  has empowered the government to construct number of jails, machine guns, upgrade intelligence securities which stands for protecting TPLF rather than protecting the country and its people. We can refer to the near occasion where world bank interest for auditing the fund released for Ethiopia has been rejected by current prime minister Hailemariyam Desallege.  I believe this is tangible evidence to question the transparency of the government. 

Therefore, many youth will try to find their way out for freedom by hock or by crock. Even if it means traveling one of the most dangerous journeys in the world risking ones own life. Sadly, until Ethiopia is free from this tyran, ears and eyes of Ethiopians along with the rest of the world will keep on witnessing the consequences of the causes and Ethiopia will keep on losing children day by day.
 
 
 
 
 

ማየት ማመን ነው በሚል የኢትዮጵያውያንን የስደት ስቃይ የሚያሳይ የፎቶ ኤግዚብሽን እና የቪዲዮ ቅንብር በኖርዌ ኦስሎ ከተማ ተካሄደ

 

ፌብሩዋሪ 17, 2014
የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌ የሴቶችና ወጣቶች ክፍል በሐገራችን ኢትዮጵያ የሰዎች የህገወጥ ዝውውርን በተመለከተና ሰዎች ከሃገራቸው ለምን እንደሚሰደዱ እንዲሁም የስደትን አስከፊነት የሚያሳይ የፎቶ ኤግዚብሽንና ቪዲዮ በDiakonhjemmet university college Oslo February 14, 2014 ለኖርዌጅያንና የተለያየ ሐገር ዜግነት ላላቸው ተማሪዎች አቀረቡ።

ይህ የፎቶ ኤግዚብሽን ዋና አላማው በሐገራችን ኢትዮጵያ በወያኔ የአገዛዝ ዘመን የህገወጥ የሰዎች ዝውውር ቁጥሩ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ በመምጣቱና ዜጎች በሐገራቸው ለመኖር የሚያስችላቸው መልካም አስተዳደር ስለሌለ የሰብአዊ መብት ጥሰቱ ከእለት ወደ እለት እየጨመረ በመምጣቱ ዜጎች የወያኔ አባል ካልሆኑ በስተቀር ተምረው የስራ እድል ስለማያገኙ፤ የመናገርና የመፃፍ መብታቸው በመገደቡ፤ ዜጎች ያለምንም ቅድመ ሁኔት መሬታቸውን እየተነጠቁ ለውጭ ሐገር ባለሃብቶች በመሸጡ  ተለዋጭ ነገር ሳያገኙ ለጎዳና ህይወት በመዳረጋቸው፤ በዘራቸው ምንክያት በሚደርስባቸው ተፅኖ  እንዲሁም በፖለቲካ አመለካከታቸው በሚደርስባቸው ከፍተኛ እስር፤ ግርፋትና እንግልት ሳቢያ ሐገራቸውን ለቀው ለመሰደድ ይገደዳሉ። ገዢው መንግስት ህጋዊ የሚላቸው ነገር ግን ህጋዊ ያልሆኑ 250 ኤጀንሲዎችን አቋቁሞ ፍቃድ በመስጠት የዜጎች ሽያጭ በስፋት እንዲያከናውኑ እያደረገ ይገኛል። እነኚህ ኤጀንሲ ተብዬዎች በአብዛኛው እድሜያቸው ለስራ ያልደረሱ ህፃናት ልጆችን ሳይቀር በገጠሪቱ የሃገራችን ክፍል የሚገኙ ወገኖቻችንን በመመልመል የራሳቸውን ኪስ ለማደለብ ለሽያጭ ያቀርባሉ።

ሰዎች ከሐገራቸው እንዲሰደዱ ዋናውን ሚና እየተጫወተ ያለው አምባገነኑ የወያኔ መንግስት ሲሆን እነዚህ ስደተኞች በመንገድ ላይ የሰውነት ብልታቸው ከውስጣቸው እየተወሰደ ሲሽጥ፤ በየመንገዱ ሲሞቱ፤ ሴቶች እህቶቻችን ተገደው ሲደፈሩ፤ ሲደበደቡ፤ የፈላ ውሃና ዘይት በላያቸው ሲደፋ፤ ከፎቅ ተወርውረው ሲሞቱ፤ በየኢምባሲው ደጃፍ ሲጎተቱ፤ አእምሮአቸውን ስተው በየጎዳናው እራቁታቸውን እየሄዱ መሳለቂያ ሲሆኑ በየሃገሩ አምባሳደር ተብለው የተወከሉት ግን ምንም አይነት ወገናዊ ስሜት የሌላቸው በመሆኑ ለወከሉት ህዝብ ከለላ መስጠት ሳይችሉ በተቃራኒው ለአረቦቹ ወግነው ሲናገሩ ይታያሉ። ሐገር ውስጥም ለሚደረገው ህገወጥ ዝውውር ገዢው ፓርቲ ትኩረት ሰጥቶ ባለመከታተሉ ወይም እያየ ዝም በማለቱ ሰዎች በኮንቴነር እንደ እቃ እየታጨቁ የብዙዎች ህይወት ማለፉ ይታወቃል። እነኚህ ከላይ የጠቀስናቸው ችግሮች በሙሉ እየተፈፀመብን ያለው በአምባገነኑ የወያኔ መንግስት መሆኑን ለአለም ለማጋለጥ ማየት ማመን ነው በሚል የወገኖቻችንን ስቃይ ከሐገር ሲወጡ ጀምሮ በመንገድና በደረሱበት ቦታ ሁሉ የሚደርስባቸውን ስቃይና እንግልት የሚያሳየውን የፎቶ ኤግዚብሽን እና ቪዲዮ ፕሮግራም ለማቅረብ የወሰነው።

ዝግጅቱ በኖርዌጅያን የሰአት አቆጣጠር ከጠዋቱ 08፤45 በትምህርት ቤቱ መምህር እና በእኛ በኩል በዶ/ር ሙሉአለም አዳም የመክፈቻ  ንግግር ሲሆን፤ በመቀጠል ተማሪዎቹ ፎቶዎቹን እየተዘዋወሩ የተመለከቱ ሲሆን አዘጋጆቹም ስለፎቶዎቹ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ከ15 ደቂቃ እረፍት በኋላ የቪዲዮ ፕሮግራም የቀረበ ሲሆን ይህ ቪዲዮ መምህራኑን ጨምሮ ተማሪዎቹን ያስለቀሰ ሲሆን አንዳንዶቹ ለማየት አቅም በማጣታቸው አዳራሹን ለቀው የወጡም ነበሩ ከቪዲዮ በኋላ ተማሪዎቹ የተሰማቸውን ስሜት ሲገልፁ መንግስታችን በዚህ የሰዎች ንግድ ውስጥ መሳተፉ ያሳዘናት መሆኑን አንዲት ተማሪ ገልፃለች። አዘጋጅ ወጣቶችም የኖርዌጂያን መንግስት ለኢትዮጵያ  የሚሰጠውን ገንዘብ ማቆም እንዳለበትና የወያኔ መንግስት የሚያገኘውን የእርዳታ ገንዘብ መሳሪያ ለመግዛት እና ህዝቦችን ለመጨቆን እየተጠቀመበት በመሆኑ በስልጣን ላይ እንዲቆይ እገዛ እያደረጉ በመሆኑ እኛ በሃገራችን ዲሞክራሲያዊ ለውጥ ለማምጣት እና ይህንን ጨቋኝ   አገዛዝ ለመጣል በምናደርገው ትግል እንቅፋት ሆኖ ያስቸገረን በመሆኑ የኖርዌጂያን ሰዎች የሚለግሱት ገንዘባቸው ለምን ተግባር እንደሚውል እንዲያውቁና ተማሪዎቹም መንግስታቸውን እንዲጠይቁ እንዲሁም ለሚያውቋቸው ሁሉ ያዩት እንዲያስረዱላቸው ጠይቀዋል።

በመጨረሻም መምህራኑ ለአዘጋጆቹ ምስጋና አቅርበው ፕሮግራሙ በኖርዌጅያን የሰአት አቆጣጠር 11፡00
ተጠናቋ። እኛም አዘጋጆቹ ለወደፊት ሐገራችን ከአምባገነኖች ነፃ እስከምትወጣ ድረስ የወያኔን ትውልድ የማጥፋት ሴራ በማጋለጥ እስከመጨረሻው እንደምንሰራ ለመግለፅ እወዳለሁ። ዝግጅቱን ለመመልከት እዚህ ይጫኑ። 
 

Saturday, February 15, 2014

የሱዳን መንግስት ኢትዮጵያውያንን ከመኖርያ ቤታቸው በኣንድ ሳምንት ውስጥ እንዲለቁ ማዘዙ ታወቀ፡፡..



የሱዳን መንግስት ተግባር እየተፈፀመ ያለው በምንሊክና በእንግሊዝ መንግስታት ድንበር ብለው ከከለሉት ቦታ ፷ ኪሎሜትር ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ገብቶ የሚገኝ ንጉዲ ከሚባል የኢትዮጵያ ሉኣላዊ ግዛት እንደሆነ የሑመራ ኑዋሪዎች ገልፀዋል፡፡ በእንግሊዝና ምንሊክ ግዜ እንደ ተፈጥሮኣዊ ድንበር ተደርጎ የነበረው ቦታ ባህረ ሰላም የተባለ ሃይቅ እንደሆነ የገለፁት ኑዋሪዎቹ ኣሁን የሱዳን መንግስት ግዛቴ ነው ልቀቁልኝ እያለ ያለው ከድንበሩ ወደ ኢትዮጵያ ፷ ኪሎሜትር ወደ ውስጥ ገብታ ከምትገኝ ንጉዲ የተባለች መንደር ኑዋሪ የሆኑት ኢትዪጵያውያንን ነው፡፡

ከቅርብ ኣመታት ወዲህ የሱዳን መንግስት ከባህረ ሰላም ወደ ውስጥ እየገባ ለእርሻ ልማት የሚውሉ ግድቦች እየገነባ እንዳለና የኢትዮጵያ መንግስት የሃገራችን መሬት እየተወረረ እያየ እነዳላየ መሆን ከማስገረም ኣልፎ እንዳበሳጫቸው ይገልፃሉ፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ ሰሙኑን ሰለ ኢትዮ፡ ሱዳን የድንበር ጉዳይ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ተጠይቀው የሰጡት ምላሽ ምንም የተፈጠረ ኣዲስ ነገር እንደሌለ መግለፃቸው በመንግስት የነበራቸው እምነት እንዲጠራጠሩ ማድረጉን ያብራራሉ፡፡

ከሑመራ ገዳሪፍ የሚወስደው የኣስፋልት መንገድ ግንባታ ኢትዮጵያ እንድታቆም በሱዳን የኣካባቢው ኣስተዳዳሪዎች ጠይቀው ስራው ቆሞ እንደነበርም ያክላሉ፡፡ የኢትዮጵያና የሱዳን መንግስታት በድንበር ጉዳይ በድብቅ ተደራድረው ሱዳን ከ፴ እስከ ፷ ኪሎሜትር ከኢትዮጵያ መሬት እንደተሰጣት ሲገለፅ መኖሩ የሚታወስ ነው፡፡

ዓረና ከሑመራና ኣከባቢዋ ኑዋሪ ህዝብ ውይይት ለማድረግ በጠራው ህዝባዊ ስብሰባ ህዝቡ በጉጉት ጠብቆ እንደነበር፣ የድንበር ጉዳዩ መፍትሄ እንዲያገኝ ተፅእኖ ያደርጋል ብለው ተስፋ ሲያደርጉ መንግስት ስብሰባው እንዳይካሄድ መደረጉ እንዳሳዘናቸው ገልፀዋል፡፡ ይህ የተደረገውም መንግስት የህዝቡ መነሳሳት ኣይቶ እንደ ሆነ ብቁጭት ይገልፃሉ፡፡
እነዚህ ከመኖርያ ቤታቸውና ከሃገራቸው በባእድ ሃገር መንግስት ሊፈናቀሉ ቀነ ገደብ የተሰጣቸው ዜጎች ሳይንገላቱና ሳይፈናቀሉ ልንደርሰላቸው ይገባል፡፡
እንደነ ኣፄ ዮውሃንስ የመሰሉ ሃገር ወዳድ ዜጎች ውድ ሂወታቸው የሰዉለት ዳር ድንበር ለማስከበር መላ ኢትዮጵያዊ በኣንድነት መነሳት የግድ ይለናል።